FT ኢትዮጵያ ቡና 3-0 ወላይታ ድቻ
47′ 50′ መስኡድ መሀመድ 90+3′ ጋቶች ፓኖም
ተጠናቀቀ!
ጨዋታው በኢትዮጵያ ቡና 3-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
ጎልልል!!!
90+3′ ጋቶች ፓኖም ከቅጣት ምት በቀጥታ የመታው ኳስ ወደ ግብነት ተቀይሯል፡፡ 3-0
የተጫዋች ለውጥ – ቡና
85′ አማኑኤል ዮሃንስ ወጥቶ ሳላምላክ ተገኝ ገብቷል፡፡
80′ ኢትዮጵያ ቡና በዝግታ በመቀባበል ወደ ድቻ የግብ ክልል ለመድረስ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ድቻዎች በአንፃሩ በራሳቸው የሜዳ ክልል ተገድበዋል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ድቻ
76′ በዛብህ መለዮ ወጥቶ አላዛር ፋሲካ ገብቷል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ቡና
73′ አህመድ ረሺድ ወጥቶ አስናቀ ሞገስ ገብቷል፡፡
70′ አክሊሉ ዋለልኝ ከቅጣት ምት በቀጥታ የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡
65′ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች በስልክ ብርሀን ደማቅ ትርኢት እያሳዩ ይገኛሉ፡፡
ቢጫ ካርድ
62′ አህመድ ረሺድ በአናጋው ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ድቻ
60′ ጸጋዬ ብርሀኑ ወጥቶ አማኑኤል ተሾመ ገብቷል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ድቻ
52′ ዮሴፍ ድንገቱ ወጥቶ ጥላሁን በቶ ገብቷል፡፡
ቢጫ ካርድ
51′ መስኡድ ማልያውን አውልቆ ደስታውን በመግለፁ ቢጫ ካርድ ተመልክቷል፡፡
ጎልልል!!! ቡና
50′ ከመስመር የተሻገረውን ኳስ መስኡድ በግንባር በመግጨት በድጋሚ አስቆጥሯል፡፡ 2-0
ጎልልል!!! ቡና!
47′ መስኡድ መሀመድ ከሳጥኑ ጠርዝ የግብ ጠባቂውን አቋቋም ተመልክቶ ማራኪ ግብ በማስቆጠር ቡናን ቀዳሚ አድርጓል፡፡
ተጀመረ!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡
የእረፍት ሰአት ለውጥ
አቡበከር ነስሩ ወጥቶ አክሊሉ ዋለልኝ ገብቷል፡፡ በለውጡ ምክንያት አማኑኤል ወደ መስመር አጥቂነት ፣ ሳኑሚ ወደ መሀል አጥቂነት ሲሸጋገሩ አክሊሉ የተከላካይ አማካይነቱን ሚና ይዟል፡፡
እረፍት!
የመጀመርያው አጋማሽ ያለ ግብ ተጠናቋል፡፡
38′ የቡና ቅብብል የድቻ ፍጹም ቅጣት ምት ክልል ጋር ሲደርስ በተደጋጋሚ እየተቋረጠ ይገኛል፡፡ በዚህም ከርቀት ለመሞከር ጥረት እያደረጉ ይገኛል፡፡
31′ መስኡድ መሀመድ ከአማኑኤል ጋር አንድ ሁለት ተቀባብሎ ከሳጥኑ ጠርዝ የሞከረው ኳስ በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡
24′ አብዱልከሪም ያሻማውን የማዕዘን ምት ወንድይፍራው በግንባሩ ገጭቶ በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡
23′ ሁለቱም ቡድኖች ከመሀል ሜዳ ያለፈ እንቅስቃሴ ማሳየት አልቻሉም፡፡
15′ ኢትዮጵያ ቡና በድቻ የሜዳ አጋማሽ አመዝኖ ኳሶችን በመቀባበል የተከላካይ መስመሩን ለማስከፈት ጥረት እያደረገ ነው፡፡ በአንጻሩ አመዛኞቹ የድቻ ተጫዋቾች ከኳስ ጀርባ በመሆን እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡
8′ አብዱልከሪም መሀመድ ከርቀት የመታውን ኳስ ወንድወሰን በቀላሉ ተቆጣጥሮታል፡፡
4′ በዛብህ መለዮ በሳጥኑ ቀኝ መስመር የሞከረው ኳስ በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡
2′ ጋቶች ፓኖም ከርቀት የመታው ኳስ ኢላማውን ስቶ ወጥቷል፡፡
ተጀመረ!
ጨዋታው በወላይታ ድቻው ተመስገን ዱባ አማካይነት ተጀምሯል፡፡
ኢትዮጵያ ቡና አሰላለፍ
99 ሀሪሰን ሄሱ
15 አብዱልከሪም መሀመድ – 16 ኤፍሬም ወንድወሰን – 5 ወንድይፍራው ጌታሁን -13 አህመድ ረሺድ
8 አማኑኤል ዮሀንስ – 3 መስኡድ መሀመድ – 25 ጋቶች ፓኖም
14 እያሱ ታምሩ – 10 አቡበከር ናስር – 11 ሳሙኤል ሳኑሚ
ተጠባባቂዎች
50 ጁቤድ ኡመድ
19 አክሊሉ ዋለልኝ
17 አብዱልከሪም ሀሰን
18 ሣለምላክ ተገኝ
7 ሳዲቅ ሴቾ
21 አስናቀ ምገስ
30 ሚኪያስ መኮንን
የወላይታ ድቻ አሰላለፍ
1 ወንድወሠን አሸናፊ
27 ሙባረክ ሽኩር – 28 ውብሸት አለማየሁ – 24 ተክሉ ታፈሰ
22 አረጋኸኝ ለማ – 2 ፈቱዲን ጀማል – 4 ዮሴፍ ደንገቶ – 7 አናጋው ባደገ
17 በዛብህ መላይ – 23 ፀጋዬ ብርሃኑ – 15 ተመስገን ዱባ
ተጠባባቂዎች
1 መሳይ ቦጋለ
8 አማኑኤል ተሾመ
19 አላዛር ፋሲካ
13 ዳግም በቀለ
20 አብዱልሰመድ አሊ
18 አሳምነው አንጀሎ
26 ጥላሁን በቶ
11:20 በግራ ጎል ጀርባ ካለው ክፍል በቀር ስታድየሙ በደጋፊዎች ተሞልቷል፡፡
11:15 ሁለቱ ቡድኖች አሟሙቀው ወደ መልበሻ ክፍል ተመልሰዋል፡፡
10:45 የሁለቱም ቡድን ተጫዋቾች እና ለማሟሟቅወደ ሜዳ ወጥተዋል፡፡
ደረጃ
ኢትዮጵያ ቡና በ32 ነጥቦች 5ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ወላይታ ድቻ በ22 ነጥቦች 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
ያለፉት 3 ጨዋታዎች አቋም
ኢትዮጵያ ቡና | አሸነፈ | አቻ | ተሸነፈ
ወላይታ ድቻ | ተሸነፈ | አቻ | ተሸነፈ
ሰላም ክቡራት እና ክቡራን !
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 21ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ከ ወላይታ ድቻ አዲስ አበባ ስታድየም ላይ በ11:30 ይካሄዳል፡፡ ሶከር ኢትዮጵያም የጨዋታውን አጠቃላይ እንቅስቃሴ በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ወደ እናንተ የምታደርስ ይሆናል፡፡
መልካም ቆይታ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር!