የአሰልጣኞች አስተያየት | ኢትዮጵያ ቡና 3-0 ወላይታ ድቻ 

አሰልጣኝ ገዛኸኝ ከተማ – ኢትዮጵያ ቡና

ስለ ጨዋታው

“ጨዋታው ጥሩ እንቅስቃሴ የታየበት ነበር፡፡ወላይታ ድቻ ጠንካራ ቡድን ነው፡፡በተለይ በመጀመሪያው አጋማሽ ወላይታ ድቻዎች ጥብቅ መከላከልን መርጠው ነበር እኛም ይህንን ስለተረዳን በሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ታክቲክ ለውጥ አድርገን ከጥሩ ጨዋታ ጋር የምንፈልገውን ሶስት ነጥብ ማግኘት ችለናል፡፡”

አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ – ወላይታ ድቻ

ስለ ጨዋታው

“በመጀመሪያው አጋማሽ በጥሩ መልኩ ተደራጅተን መከላከል ችለናል ነገርግን በምናጠቃበት ወቅት በልጆቼ ላይ የራስ መተማመን ችግር ይታይ ነበር፡፡በሁለተኛው አጋማሽ እነሱ በጣም ከኛ የተሻሉ ነበሩ እኛ ደግም በአንጻሩ በመከላከሉ ረገድ ጥሩ አልነበርንም ከዚህም የተነሳ በቀላሉ ግቦችን አስተናግደን ልንሸነፍ ችለናል፡፡”

ሰለ የዘንድሮው አመት የወላይታ ድቻ ከወትሮው ተዳክሞ መቅረብ ምክንያት

“ከዚህ ቀደም በነበሩት አመታት እንዳሁኑ በቀላል ግቦች አይቆጠሩብንም ነበር እኛም ግቦችን እናስቆጥር ነበር ፤ እነዚህ ጠንካራ ነገሮች ዘንድሮ አብረውን የሉም፡፡ በራስ መተማመናችን ወርዷል እንዲሁም በዋነኝነት በመከላከል አደረጃጀት በኩል ክፍተቶች አሉብን፡፡በቀጣይ እነዚህ ችግሮች አርመን ካለንበት አደገኛ ቀጠና ለመውጣት ጠንክረን አንሰራለን፡፡”

ስለ ወራጅነት ስጋት መደቀን

“በሊጉ በቀጣይ የምናደርጋቸው ዘጠኝ ጨዋታዎች ለእኛም ሆነ ለሌሎች እኛን መሰል ቡድኖች እጣፈንታችንን የሚወስኑ ይሆናል፡፡”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *