በሴቶች ፕሪምየር ሊግ 16ኛ ሳምንት የዛሬ ውሎ ባንክ ፣ ሀዋሳ እና ኤሌክትሪክ አሸንፈዋል

 

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ዛሬ በተደረጉ ጨዋታዎች ሲጀምር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ ኤሌክትሪክ እና ሀዋሳ ከተማ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡

ምድብ ሀ

አዳማ ላይ አዳማ ከተማ ከድሬዳዋ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ 2-2 በሆነ አቻ ውጤት ተፈፅሟል፡፡ አዳማ ከተማ እስከ ቅርብ ሳምንታት ድረስ አስገራሚ ግስጋሴ በማድረግ ደደቢትን እግር በእግር መከተል ችሎ የነበረ ቢሆንም በተከታታይ በጣላቸው ነጥቦች ከመሪው ጋር ያለው ልዩነት እየሰፋ ይገኛል፡፡

ወደ ባህርዳር ያመራው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጥረት ኮርፖሬትን ጤናዬ ወመሴ ባስቆጠረችው ብቸኛ ግብ ታግዞ 1-0 አሸንፏል፡፡ ኤሌክትሪክ በሊጉ ከፍተኛ መሻሻል እያሳዩ ከሚገኙ ክለቦች አንዱ መሆኑን ቀጥሏል፡፡

[table id=233 /]

[league_table 18073]

 

ምድብ ለ

አዲስ አበባ ስታድየም ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስን የገጠመው ሀዋሳ ከተማ 1-0 በማሸነፍ በጠንካራ አቋሙ መቀጠል ችሏል፡፡ የሀዋሳን ብቸኛ የድል ጎል ያስቆጠረችው አይናለም አሳምነው ነች፡፡ አይናለም በሊጉ ያስቆጠረቻቸውን ግቦች 21 በማድረስ ሎዛ አበራን እየተከተለች ትገኛለች፡፡

የዚህን ጨዋታ ተከትሎ 10:00 ላይ የተካሄደው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አዲስ አበባ ከተማ ጨዋታ በንግድ ባንክ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ የመጀመርያው አጋማሽ ለባንክ ታሪኳ ደቢሶ ለአአ ከተማ አስራት አለሙ ባስቆጠሯቸው ጎሎች 1-1 ሲጠናቀቅ ከእረፍት መልስ ረሂማ ዘርጋ ከርቀት አክርራ በመምታት ባስቆጠረችው ግሩም ግብ ታግዞ ንግድ ባንክ 3 ነጥቦች ሰብስቧል፡፡

በዚህ ምድብ አርባምንጭ ላይ በተደረገ ጨዋታ አርባምንጭ ከተማ ከ ሲዳማ ቡና 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

 

 

[table id=243 /]

[league_table 18083]

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *