ቻን 2016፡ ኢትዮጵያ ከኬኒያ ሊቢያውያን ዳኞች ይዳኙታል

ሩዋንዳ ለምታስተናግደው የቻን ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ ከኬኒያ ጋር የተደለደለው ኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ሰኔ 14 ለሚያደርገው ጨዋታ ሊቢያውያን ዳኞች እንደተመደቡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን አስታውቋል፡፡ የመሃል ዳኛ መሃመድ ራጋብ ኦማራ ከሊቢያ ሲሆኑ ረዳቶቻቸው ፉአድ መሃመድ ኤል-መግራቢ እና ዋሂድ አል-ጃዋም ናቸው፡፡ አራተኛው ዳኝ ዋሂድ ታሙኒ ሳላ ከሊቢያ ሁነዋል፡፡ የጨዋታው ኮሚሽነር ማርኮ አብርሃም ላዶ ከደቡብ ሱዳን ናቸው፡፡ ጨዋታው ዕሁድ ሰኔ 14 2007 በ10፡00 በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተነግሯል፡፡

ያጋሩ