የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬም ሲቀጥሉ ደደቢት የምድብ ሀ አሸናፊ መሆኑን ያረጋገጠበትን ድል አስመዝግቧል፡፡ ጌዲኦ ዲላም በአስደናቂ የውድድር ዘመን ጉዞው ቀጥሏል፡፡
በምድብ ሀ መሪው ደደቢት ከመከላከያ ያደረጉት ጨዋታ በደደቢት 4-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ለሰማያዊዎቹ ሎዛ አበራ 3 ግቦች አስቆጥራ ሐት-ትሪክ ስትሰራ ብርቱካን ገብረክርስቶስ ቀሪዋን ግብ አስቆጥራለች፡፡ ድሉን ተከትሎ ደደቢት 43 ነጥቦችን በመሰብሰብ ከተከታዩ አዳማ ከተማ 11 ነጥቦች መራቅ የቻለ ሲሆን 3 ጨዋታዎች እየቀሩት የምድብ ሀ አሸናፊ መሆኑን አረጋግጧል፡፡
የአምናው ቻምፒዮን ደደቢት በቀጣይ የምድብ ለ አሸናፊ ሆኖ የሚያጠናቅቀውን ክለብ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ይጫወታል፡፡
በጨዋታው ሶስት ጎሎችን ያስቆጠረችው ሎዛ አበራ የግብ መጠኗን 29 በማድረስ ለ3ኛ ተከታታይ አመታት ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆና ለማጠናቀቅ ተቃርባለች፡፡
[table id=233 /]
[league_table 18073]
በምድብ ለ ወደ አዲስ አበባ የተጓዘው ጌዲኦ ዲላ ዳግም ድል አስመዝግቧል፡፡ ልደታን የገጠመው ጌዲኦ ዲላ 1-0 በመርታት 3ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡ በሊጉ ዘንድሮ አእየተሳተፈ የሚገኘው ጌዲኦ ዲላ አስደናቂ የውድድር ዘመን ማሳለፉን አሁንም ቀጥሏል፡፡
[table id=243 /]
[league_table 18083]