ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮጵያ ቡና – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

 FT ቅዱስ ጊዮርጊስ   1-1  ኢትዮጵያ ቡና 

 66′ ሳላዲን ሰይድ (ፍቅም)     18′ ኢኮ ፌቨር

የአመቱ ሁለተኛው የሸገር ደርቢ በ 1 ለ 1 የአቻ ውጤት ተጠናቋል !

90′ ጭማሪ ደቂቃ 2 !

የተጨዋች ቅሪዎች

85′ ኢትዮጵያ ቡና

ያቡን ዊልያም በአማኑኤል ዮሀንስ

82 ኢትዮጵያ ቡና

ሣለምላክ ተገኝ በአስቻለው ግርማ

81′ ቅዱስ ጊዮርጊስ

ራምኬል ሎክ በፕሪንስ ሰቨሪን
77′ ኒኪማ ከቀኝ መስመር ያሻማውን ኳስ አዳነ በግንባሩ ሞክሮ ሀሪሰን ይዞበታል ።

74′ ከቀኝ መስመር ኒኪማ የተሻማውን ኳስ ፕንስ ከቅርብ ርት አግኝቶ ቢሞክርም ወደላይ ተነስቶበታል ።

73 ‘ ከቅጣት ምት የተሻማውን ኳስ አስቻለውጨርፎት ዘሪሁን ከመስመር ላይ ለጥቂት ይበታል ።

71′ ከመሀል የተሻማው ኳስ ኤፍሬምን ሲያመልጠው ሳላዲን አግኝቶ ቢሞክርም ወደውጪ ወጥቶበታል ።

70’ ካታንጋ አካባቢ አለመረጋጋት ይታያል ።
70′ የተጨዋች ለውጥ ኢትዮጵያ ቡና
አብዱልከሪም ሀሰን በመስዑድ መሀመድ ተቀይሮ ገብቷል 

68′ አስቻለው ግርማ ከርቀት የሞከረው ኳስ ወደውጪ ወጥቷል።

66′ ጎል ቅዱስ ጊዮርጊስ ሳላዲን ሰይድ 
ሳላዲን ሰይድ ሳጥን ውስጥ በተሰራበት ጥፋት ምክንያት የተሰጠውን የፍፁም ቅጣት ምት ራሱ አስቆጥሯል ።

64′ ቡናዎች አሁንም ጥሩ የመልሶ ማጥቃት ዕድል አግኝተው በመጨረሻ እያሱ ከቀኝ መስመር ያሻማውን ኳስ መስዑድ በግንባሩ ለማስቆጠር ሞክሮ ሳይሳካለት ሲቀር አስቻለው በቮሊ አንክኖታል ።61′ ሳላዲን ከመሀል የተሻገረለት ኳስ ከሀሪሰን ጋር ቢያገናኘውም በሀሪሰ አናት ላይ ከፍ አድርጎ ለማስቆጠር ሲሞክር ሀሪሰን በቀላሉ ይዞበታል ።
59′ በግምት ከ 30 ሜትር በግቡ ትይዩ የተሰጠውን ቅት ምት አበባው በድንቅ ሁኔታ መቶ ሀሪሰን በቅልጥፍና አድኖበታል ።

56′ ጊዮርጊሶች ከመስመር የሚሰነዝሩት ጥቃት ቀጥሏል ። ቡናዎች ወደመከላከሉ ያደሉ ይስላሉ ሆኖም ጥሩ የመልሶ ማጥቃት ዕድችን መፍጠር ችለዋል ። ይህ አጨዋወታቸውም ሳኑሚ ላይ የተመረኮዘ ይስላል ።

53 ሳላዲን ከአዳነ ጥሩ ኳስ ደርሶት ከግቡ ጥቂት ርቀት ላይ ያገኘውን ዕድል አክርሮ ባለመምታቱ አምክንታል ።

50′ ጊዮርጊሶች የተሻለ እያጠቁ ይገኛሉ ። ተደጋጋሚ የመስመር ኳሶችንም እየጣሉ ነው ሆኖም በማጥቃት ጊዜ ወደቡና ሜዳ መሳባቸው ለ ኢትዮጵያ ቡና የመልሶ ማጥቃት እድሎችን እየፈጠረ ይገኛል ።

49′ ፕሪንስ ከቀኝ መስመር ጥጥሩ ኳስ አሻምቶ ኤኮ ሊያወጣ ሲሞክር ኳስ ወደራሱ ግብ ሄዳ ለጥቂት ወጥታለች ። ጨዋታው በማዕዘን ምት ቀጥሏል ።
47′ አዳነ በመሀል አማካይነት ጨዋታውን ሲቀላቀል ኒኪማ ወደ መስመር በመውጣት የአቡበከርን ቦታ ወስዷል ።

46′ ሁለተኛው አጋማሽ በሳላዲን ሰይድ አማካይነት ሲጀመር አዳነ ግርማ አቡበከር ሳኒን ተክቶ ወደሜዳ ገብቷል ።
የመጀመሪያው አጋማሽ በኢኮ ብቸኛ ግብ ተጠናቋል !

45′ ጭማሪ ደቂቃ 3 !

40′ እስካሁን ባለው እንቅስቃሴ የቡድኖቹ የመስመር ተከላካዮች ጥንቃቄን በመምረጥ ወደመከላከሉ አዘንብለዋል ። ሁለቱም ቡድኖች የሜዳውን የጎን ስፋት ለመጠቀም አልተቻላቸውም ።

38′ የተጨዋች ለውጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ሮበርት ኦድንካራ በዘሪሁን ታደለ ተቀይሯል ።

35′ ሮበርት ጉዳት አስተናግዶ የህክምና እርዳታ ቢደረግለትም ጨዋታውን መቀጠል አልቻለም ። 

33′ ከደቂቃ ወደ ደቂቃ ጨዋታው መቀዛቀዙን ቀጥሏል ። ሙከራ አልባ እእና የተቆራረጡ ቅብብሎች በዝተዋል ።

30′ መስዑድ በአስቻለው ላይ በሰራው ጥት የቢጫ ካርድ ተመልክቷል ።

25′ ምንስኖት ከሳጥን ውስጥ በቮሊ የሞከረውን ኳስ ኤፍሬም ተደርቦ አውጥቶበታል ።

22′ ከግቡ መቆጠር በኃላ ቡናዎች የኳስ ቁጥጥር የበላይነቱን ወስደዋል ። አሁንም ግን የተጨዋቾች ግጭት እንቀጠለ ነው ። የቅጣት ምቶችም ተደጋጋሚ ሆነዋል ።

18′ ጎል ኢትዮጵያ ቡና ኢኮ ፌቨር

መስዑድ ከማዕዘን ምት ያነሳው ኳስ በጊዮርጊስ ተከላካዮች ተገጭቶ ሲወጣ እና አብዱልከሪም በቀጥታ ሲሞክር የግቡ ቋሚ ሲመልስበት አግኝቶ ኢኮ አክርሮ ከሳጥን ውስጥ በመምታት አስቆጥሯል ። ለናይጄሪያዊው የመሀል ተከላካይ በሸገር ደርቢ ሁለተኛ ጎሉ ሆኖ ተመዝግቦለታል ።

17′ አስለው ከ መስዑድ ባጭሩ የተቀበለውን የማዕዘን ምት ሞክሮ ሮበርት ይበታል ።

11′ ፕሪንስ ያሻማውን የማዕዘን ምት ሳላዲን በግንባሩ ሞክሮ በርቀት ወደውጪ ወጥቶበታል ።

10′ እስካሁን ያለው ጨዋታ በፍጥነቱ በእንቅስቃሴ ዝግ ያለ በተደጋጋሚ ጥፋቶች የሚቋረጥ እንዲሁም በሁለቱ ሳጥኖች መሀል ላይ ያመዘነ ነው ።

7′ ሳላዲን በቡና የግብ ክልል ውስጥ አህመድን ኳስ ቀምቶ ከመሞከሩ በፊት አህመድ በድጋሜ ኳሷን ማዳን ችሏል ።

5′ አበባው ቡጣቆ ጥፋት በመስራቱ የመጀመሪያውን የቢጫ ካርድ ተመልክቷል ።

4′ ሳላዲን ሰይድ ከመሀል የተሻገረለትን ኳስ በግንባሩ ቢሞክርም ሀሪሰን በቀላሉ ይታል ።

2′ ጨዋታው በኢትዮጵያ ቡና የኳስ ቁጥጥር ከመሀል ሜዳ በጥቂቱ ወደ ጊዮርጊሶች ሜዳ አድልቶ እተካሄደ ነው ።

1′ ጨዋታው በኢትዮጵያ ቡናው ሳሙኤል ሳኑሚ አማካይነት ተጀመረ ።

09፡55 ተጨዋቾች ወደሜዳ ገብተዋል ። ሰላምታ በመለዋወጥ ላይ ይገኛሉ ። ስታድየሙ በክለቦቹ አርማ አሸብርቋል ። ከደቂቃዎች በኋላ ጨዋታው የሚጀምር ይሆናል ።

የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰላለፍ
30 ሮበርት ኦዶንካራ

2 ፍሬዘር ካሳ – 15 አስቻለው ታመነ – 12 ደጉ ደበበ (አምበል) – 4 አበባው ቡታቆ

27 አብዱልከሪም ኒኪማ – 26 ናትናኤል ዘለቀ – 23 ምንተስኖት አዳነ

18 አቡበከር ሳኒ – 7 ሳላዲን ሰይድ – 11 ፕሪንስ ሰቨሪን

ተጠባባቂዎች

22 ዘሪሁን ታደለ

13 ሳላዲን ባርጌቾ

3 መሀሪ መና

21 ተስፋዬ አለባቸው

24 ያስር ሙገርዋ

10 ራምኬል ሎክ

19 አዳነ ግርማ

የኢትዮጵያ ቡና አሰላለፍ

99 ሀሪሰን ሄሱ 

15 አብዱልከሪም መሀመድ – 16 ኤፍሬም ወንድወሰን – 4 ኢኮ ፌቨር -13  አህመድ ረሺድ

3 መስኡድ መሀመድ (አምበል)– 19 አክሊሉ ዋለልኝ –  8 አማኑኤል ዮሀንስ 

14 እያሱ ታምሩ – 11 ሳሙኤል ሳኑሚ –  24 አስቻለው ግርማ

ተጠባባቂዎች

32 ዮሐንስ በዛብህ

21 አስናቀ ሞገስ

5 ወንድይፍራው ጌታሁን

17 አብዱልከሪም ሀሰን 

18 ሣለምላክ ተገኝ 

28 ያቡን ዊልያም

10 አቡበከር ናስር

የመሀል ዳኛ 

ፌደራል ዳኛ ሰለሞን ገ/ሚካኤል

ረዳት ዳኞች 

ኢ/ል ዳኛ ትግል ግዛው 

ኢ/ል ዳኛ ክንዴ ሙሴ

አራተኛ ደኛ 

ፌደራል ዳኛ ዳንኤል ግርማይ

09፡45 ተጨዋቾቹ አሟሙቀው በመጨረስ ወደመልበሻ ክፍል አምርተዋል ።
09፡20 የተጋጣሚ ቡድኖቹ ተጨዋቾች እና የእለቱ አልቢትሮች ወደ ሜዳ ገብተው ማሟሟቅ ጀምረዋል ።

09፡00 ስታድየሙ ከካታንጋ አጋማሽ እስከ ክቡር ትሪቡን አጋማሽ ድረስ በግማሽ ተከፍሎ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች የግራውን እንዲሁም የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች የቀኙን አጋማሽ ይዘዋል ። እጅግ ደስ የሚል እግር ኳሳዊ ድባብ እተመለከትን እንኛለን ።

08፡55 ታዳጊዎቹ ጨዋታቸውን ጨርሰው ደጋፊውን በመሰናበት ከሜዳ ወጥተዋል ። 

08፡50 የቅዱስ ጊዮርጊስ የቡድን አባላትም በደጋፊዎቻቸው አቀባበል ታጅበው ወደመልበሻ ክፍል አምርተዋል ።

08፡45 የኢትዮጵያ ቡና ተጨዋቾች ወደ ስታድየሙ ደርሰዋል ። ደጋፊዎቻቸውም አቀባበል አድርገውላቸዋል ። 

08፡30 ታዳጊ ህፃናቱ ሜዳው ስምንት ቦታ ተከፍሎላቸው በጠባብ ጎሎች እርስ በእርስ እተጫወቱ ይገኛሉ ። አሁን ስታድየሙ ሙሉ ለሙሉ እየሞላ ነው ።

08፡15 የሰውነት ቢሻው እና ቤተሰቡ አካዳሚ ታዳጊ ህፃናት ሜዳው ላይ በብዛት በመግባት በዕድሜ ተከፋፍለው ኳስ በማንሸራሸር ላይ ይገኛሉ ።

08:00 ስታድየሙ ካሁኑ መሙላት ጀምሯል ። የሁለቱ ክለቦች ደገፊዎች በዜማ በመበሻሸቅ በስታድየሙ አስደሳች ድባብ ፈጥረዋል ። 

ወቅታዊ ሁኔታ

ቅዱስ ጊዮርጊስ

ደረጃ – 2ኛ

የ5 ጨዋታ አቋም | አሸ – ተሸ – ተሸ – አሸ – አቻ

ኢትዮጵያ ቡና

ደረጃ – 5ኛ

የ5 ጨዋታዎች አቋም | አሸ – አቻ – ተሸ – አሸ – ተሸ


የእርስ በእርስ ግንኙነት እውነታዎች

– ሁለቱ ቡድኖች በሊጉ 35 ጊዜ ሲገናኙ ቅዱስ ጊዮርጊስ 18 በማሸነፍ ቀዳሚ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ቡና 7 ሲያሸንፍ  10 ጨዋታዎች ደግሞ በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ 48 ጎል ሲያስቆጥር ኢትዮጵያ ቡና 21 አስቆጥሯል፡፡

– በመጀመርያው ዙር ባደረጉት ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና በኢኮ ፊቨር ግብ 1-0 ማሸነፉ ይታወሳል፡፡


ሰላም ክቡራት እና ክቡራን !

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 23ኛ ሳምንት በጉጉት የሚጠበቀው የሸገር ደርቢ በቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና መካከል በአአ ስታድየም 10:00 ላይ ይካሄዳል፡፡ ሶከር ኢትዮጵያም የጨዋታውን አጠቃላይ እንቅስቃሴ በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ወደ እናንተ የምታደርስ ይሆናል፡፡

መልካም ቆይታ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር!

3 Comments

  1. Please try to update the progress of the game a bit faster. I tried to refresh the page but it still on 7′ update though the game is on for about 30’th minute

Leave a Reply