የሴቶች ፕሪምየር ሊግ 17ኛ ሳምንት ዛሬ ሲጀመር ደደቢት አሸንፏል

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ 17ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታዎች ደደቢት ሲያሸንፍ ንፋስ ስልክ ከ ቡና አቻ ተለያይተዋል፡፡

08:30 ላይ በአዲስ አበባ ስታድየም ኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚን የገጠመው ደደቢት 4-1 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል፡፡ ለደደቢት ብርቱካን ገብረክርስቶስ ሁለት ጎሎችን ስታስቆጥር ሰናይት ባሩዳ እና ሰናይት ቦጋለ ቀሪዎቹን አስቆጥረዋል፡፡ መዲና ጀማል ደግሞ የአካዳሚን ብቸኛ ጎል ማስቆጠር ችላለች፡፡

ደደቢት ባለፈው ሳምንት መከላከያን 4-0 በማሸነፍ የምድብ ሀ አሸናፊ መሆኑን ማረጋገጡ የሚታወስ ነው፡፡

ቀጥሎ በ10:30 ላይ የተደረገው የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡

ንፋስ ስልክ ላፍቶ ዘነበች ዘመዱ ባስቆጠረችው የቅጣት ምት ጎል ቀዳሚ ቢሆንም ማዕድን ሳህሉ ኢትዮጵያ ቡናን አቻ አድርጋለች፡፡ በጨዋታው ንፋስ ስልክ ላፍቶ መሪነቱን የሚያሰፋበት የፍጹም ቅጣት ምት አግኝቶ ግብ አስቆጣሪዋ ዘነበች መትታ ሳትጠቀምበት ቀርታለች፡፡

ምድብ ሀ

ምድብ ለ

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *