ድሬዳዋ ከተማ ላይ የተላለፈው ቅጣት በጊዜያዊነት ተነሳ

 

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ድሬዳዋ ከተማ ላይ የተጣለውን አንድ ጨዋታ በዝግ የማካሄድ ቅጣት በጊዜያዊነት ማንሳቱ ታውቋል፡፡

ድሬዳዋ ከተማ እግርኳስ ክለብ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በተደረገው ጨዋታ ላይ ደጋፊዎቹ ባሳዩት ያልተገባ ድርጊት ምክንያት የ75,000 ብር እና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ በዝግ ስታድየም እንዲጫወት ተወስኖበት የነበረ ቢሆንም ክለቡ ይግባኝ በመጠየቁ ቅጣቱ ለጊዜው መነሳቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

የቅጣቱ ተግባራዊነት በየትኛው ጨዋታ እና አግባብ እንደሚፈፀም ፌዴሬሽኑ ያለው ነገር የለም፡፡

በድሬዳዋ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ መካከል የሚደረገው የ24ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ በመጪው ሀሙስ 10:00 ላይ በድሬዳዋ ስታድየም ይካሄዳል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *