የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ 19ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ረቡዕ ሲደረጉ የምድቡ መሪዎች ከተከታዮቻቸው ያላቸውን ልየነት ያሰፉበትን ድል አስመዝግበዋል፡፡
በዚህ ሳምንት ከተደረጉት 8 ጨዋታዎች ውስጥ 3ቱ ያለምንም ግብ ሲጠናቀቁ 13 ግቦች ብቻ ተስተናግደዋል። በሜዳው አዲስ አበባ ፖሊስን የገጠመው የምድቡ መሪ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ 3-0 ውጤት አሸንፏል። ለወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ሀይሌ ፀጋዪ፣ አዲሱ ፈራሚ ቴድሮስ መንገሻ እና ከድር ሳላ ጎሎችን ያስቆጥሩ ተጨዋቾች ናቸው፡፡
በሌላ ተጠባቂ ጨዋታ ከወልዋሎ በአንድ ነጥብ አንሶ የሚገኘው መቐለ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማን መቐለ ዩኒቨርሰቲ ሜዳ ላይ አስተናግዶ 3-0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ የመቐለን የድል ግቦች ያሬድ ከበደ አንድ ፣ ጌድዮን ታደሰ ሁለት አስቆጥረዋል፡፡
በደረጃ ሰንጠረዡ 3ኛ የሚገኘው ባህር ዳር ከተማ ወደ አዲስ አበባ ተጉዞ ያለ ግብ አቻ በመለያየት ነጥብ ተጋርቶ ተመልሷል፡፡ በጨዎታው በርካታ ለግብ የቀረቡ ሙከራዋች የተደረጉ ቢሆንም ወደ ግብነት መለወጥ ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡ በተለይ የባህር ዳር ከተማው ኤርምያስ ዳንኤል ሁለት ጊዜ ከግብ ጠባቂው ጋር አንድ ለአንድ ተገናኝቶ የግቡ አግዳሚ የመለሰበት ሙከራዎች የሚስቆጩ ነበሩ፡፡
በሌሎች ጨዎታዋች ሰበታ ከተማ ከ አማራ ውሃ ስራ፤ ቡራዩ ከተማ ከ ለገጣፎ ለገዳዲ ያለምንም ጎል ተጠቀዋል፡፡ ኢትዮ መድን አዲስ አበባ ላይ አክሱም ከተማን አስተናግዶ 2-1 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ ወሎ ኮምበልቻ ከ ሰሜን ሸዋ ደብር ብርሃን ያገናኘው ጨዋታ በወሎ ኮምበልቻ 3-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
ውጤቶቹ በደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ ለውጥ ያላስከተሉ ቢሆንም ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ 40 መቐለ ከተማ 39 ነጥቦች በመሰብሰብ ከተከታዮቻቸው መራቅ ችለዋል፡፡