ፔትሮጀት በሽመልስ በቀለ ብቸኛ ግብ አሸንፏል

በግብፅ ፕሪምየር ሊግ የ25 ሳምንት ጨዋታዎች ቅዳሜ በተደረጉ ሶስት ጨዋታዎች ሲጀመር ዛሬ ቀትር ላይ ፔትሮጀትን ያስተናገደው ታላል ኤል ጋይሽ 1-0 በሆነ ውጤት በሜዳው ተሸንፏል፡፡

ካይሮ በሚገኘው ገዛ ኤል ሪያዳ ስታዲየም በተደረገው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ብቸኛዋን የማሸነፊያ ግብ ሽመልስ በቀለ በ16ኛው ደቂቃ በግንባሩ በመግጨት አስቆጥሯል፡፡ መሃመድ ረመዳን በቀኝ መስመር የተገኘውን ቅጣት ምት ወደ አደጋ ክልሉ ሲያሻማ ነፃ የነበረው ሽመልስ በመሃመድ ባሰም መረብ ላይ አስቆጥሯል፡፡

ፔትሮጀት ከሁለት ጨዋታዎች በኃላ ሙሉ ሶስት ነጥቦችን በሰበሰበበት ጨዋታ ከወራት በኃላ በመጀመርያው አሰላለፍ ውስጥ የተካተተው ሽመልስ በሁለተኛው አጋማሽ 60ኛው ደቂቃ ላይ በሃምዲ ፋቲ ተቀይሮ ከሜዳ ወጥቷል፡፡

ድሉን ተከትሎ ፔትሮጀት በግብፅ ፕሪምየር ሊግ 37 ነጥቦችን በመሰብሰብ ሰባተኛ ላይ ረግቷል፡፡

የሽመልስን ጎል ይመልከቱ  LINK

Leave a Reply