ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ –  ጅማ ከተማ ሲያሸንፍ ተከታዮቹ ነጥብ ጥለዋል

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 20ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ማክሰኞ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ሲደረጉ ጅማ ከተማ እና ሀዲያ ሆሳዕና ድል ቀንቷቸዋል፡፡ ሀላባ ከተማ እና ወልቂጤ ከተማ ደግሞ ነጥብ ጥለዋል፡፡

ጅማ ላይ ጅማ ከተማ ጅንካ ከተማን አስተናግዶ 5-2 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ በምድብ ለ መሪነቱን ማጠናከር የቻለበትን ውጤት አስመዝግቧል። ጅማዎችን ቀዳሚ ያደረጋቸውን ጎል በ25ኛው ደቂቃ በመጣባቸው ሙሉ አማካይነት ሲያገኙ በተከታታይም በተመስገን ገ/ኪዳን ፣ በሮባ ወርቁ እና ተዘራ አቡቴ (ሁለት) ጎሎች ታግዞ 5-2 አሸንፏል፡፡ ጅንካ ከተማ ከመሸነፍ ያልዳነበትን ጎሎች በሰምሶን እና አልዬ አማካይነት ማግኘት ችሎዋል፡፡ ጅማ በሜዳው 5-2 ሲያሸንፍ ይህ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ ነው፡፡

ከፍተኛ ትኩረት አግኝቶ የነበረው የስልጤ ወራቤ እና ሀላባ ከተማ ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተፈፅሟል፡፡ ባለፈው ሳምንት ጅማ ከተማ መሸነፉን ተከትሎ ልዩነቱን አጥብቦ የነበረው ሀለባ ከተማ በአቻ ውጤቱ መልሶ ልየዩነቱን ለማስፋት ተገዷል፡፡

ሀድያ ሆሳዕና ወደ አርሲ ነገሌ አምርቶ 1-0 አሸንፎ ተመልሷል፡፡ ደረጃውንም ወደ 3ኛ ከፍ ማደድረግ ችሏል፡፡ በተከታታይ ነጥቦች እየጣለ የሚገኘው ወልቂጤ ከተማ ፌዴራል ፖሊስን አስተናግዶ ያለ ግብ አቻ በመለያየት ከመሪው ያለውን ርቀት ወደ 5 ለማስፋት ተገዷል፡፡

በሌሎች ጨዋታዎች ወደ ሀዋሳ ያመራው ናሽናል ሴሜንት ደቡብ ፖሊስን 2-1 በማሸነፍ ከተከታታይ ሽንፈቶች አንሰራርቷል፡፡ ነገሌ ቦረና ዲላ ከተማን አስተናግዶ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ሲለያዩ ድሬዳዋ ላይ ነቀምትን ያስተናገደው ድሬዳዋ ፖሊስ 1-0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ በውድድር ዘመኑ ለመጀመርያ ጊዜ ከወራጅ ቀጠናው መውጣት ችሏል፡፡

በሻሸመኔ ከተማ እና ካፋ ቡና መካከል የተደረገው ጨዋታ እንደተጀመረ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ወደ ዛሬ የተሸጋገረ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም ጨዋታው እየተከናወነ ይገኛል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *