የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በቅርብ አመታት ከባድ የሚባለውን የቅጣት በትር ሀዲያ ሆሳዕና ላይ አሳርፏል፡፡
በ18ኛው ሳምንት ከስልጤ ወራቤ ገር በተደረገው ጨዋታ 36ኛው ደቂቃ ላይ የሀድያ ሆሳዕና ደጋፊዎች ድንጋይ በመወርወር ለ25 ደቂቃዎች እንዲቋረጥ በማድረግ ፤ ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላም ረብሻ በመፍጠር ፣ የፀጥታ ሀይሎች ላይ ጥቃት በማድረስ ፣ ዳኞች ከሜዳ እንዳይወጡ በመከልከል እና መሰል ስፖርታዊ ጨዋነት ግድፈቶች መፈጸማቸው በእለቱ ኮምሽነር ሪፖርት ከመቅረቡ በተጨማሪ የክለቡ ደጋፊዎች ዘንድሮ ብቻ ከሻሸመኔ ከተማ ፣ ወልቂጤ ከተማ እና ጂንካ ከተማ ጋር በፈጸሙት ከስፖርታዊ ጨዋነት ያፈነገጠ ተግባር በተጣለባቸው ቅጣቶች ትምህርት ሳይወስዱ በድጋሚ ወደዚህ ተግባር በመመለሳቸው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በዲሲፕሊን መመርያው ላይ የተቀመጠውን ደንብ በመጥቀስ ክለቡ ካለው ነጥብ ላይ 6 ነጥቦች እንዲቀነሱበት ሲወስን በ30 ቀናት ውስጥ ክለቡ ለደጋፊዎቹ የስፖርታዊ ጨዋነት ግንዛቤ ማስጨበጫ በመስጠት ሪፖርት እንዲያደርግ ተወስኖበታል፡፡
ሀዲያ ሆሳዕና በቅጣቱ መሰረት ከነበረው 33 ነጥብ ወደ 27 ነጥቦች ሲወርድ ደረጃውም ከ3ኛ ወደ 7ኛ አሽቆልቁሏል፡፡