ሮበርት ኦዶንግካራ ጣልያንን አሻግሮ እየተመለከተ ነው

የቅዱስ ጊዮርጊሱ ድንቅ ግብ ጠባቂ ሮበርት ኦዶንግካራ ወደ ጣልያን ክለቦች ለሚያደርገው ዝውውር በድርድር ላይ መሆኑን የኡጋንዳው ካዎዎ ድረ-ገፅ ዘግቧል፡፡ ኦዶንግካራም የመረጃውን ትክክለኝነት አረጋግጧል፡፡ ‹‹ ወኪሌ ከ2014 የአለም ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች ጀምሮ እስካሁን ከክለቦቹ ጋር ድርድር አያደረገ ነው፡፡ ›› ብሏል፡፡

‹‹ አሁን ላይ እርግጠኛ ሁኜ መናገር የምችለው ነገር የለም፡፡ በጁን ወር ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያለኝ ኮንትራት እስኪጠናቀቅ ድረስም ስለ ዝውውሩ የምናወራበት ትክክለኛ ሰአት አይደለም፡፡ ለጊዜው የምናገረው ወኪሌ ከሴሪ-ቢ (የጣልያን 2ኛው ከፍተኛ ሊግ) ክለቦች ጋር እየተነጋገረ መሆኑን ነው፡፡ ››

ከዩጋንዳው ዩአርኤ በ2003 የውድድር ዘመን አጋማሽ ቅዱስ ጊዮርጊስን የተቀላቀለው ሮበርት ኦዶንግካራ በቅዱስ ጊዮርጊስ የተሳኩ 3 አመት ተኩል ጊዜያትን አሳልፏል፡፡ {jcomments on}

ያጋሩ