ፕሪምየር ሊግ | ድሬዳዋ ከተማ ከ ወልድያ የሚያደርጉት ጨዋታ በዝግ ስታድየም ይካሄዳል

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 26ኛ ሳምንት ድሬዳዋ ከተማ ወልድያን የሚያስተናግድበት ጨዋታ በዝግ ስታድየም እንዲካሄድ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ወስኗል፡፡

በ22ኛው ሳምንት ድሬደዳዋ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ባደረጉት ጨዋታ የድሬዳዋ ከተማ ደጋፊዎች የስፖርታዊ ጨዋነት ጥሰት መፈፀማቸውን ተከትሎ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን ኮሚቴ ድሬዳዋ ከተማን 75000 ብር እና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ በዝግ ስታድየም እንዲያካሂድ ቅጣት ማስተላለፉ የሚታወስ ነው፡፡ ሆኖም ክለቡ ይግባኝ በማቅረቡ የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ጉዳዩን እስኪመለከተው ድረስ ቅጣተቱ ተግባራዊ ሳይደረግ ቆይቶ ነበር፡፡ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴው የክለቡን ይግባኝ ውድቅ ማድረጉን ተከትሎም ሰኞ ወልድያን በዝግ ስታድየም የሚያስተናግድ ይሆናል፡፡

Leave a Reply