ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | በዛሬ ጨዋታዎች ኤሌክትሪክ ሲያሸንፍ አአ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ ተጋርተዋል

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ 18ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬም በ2 ጨዋታዎች ቀጥለው ሲደረጉ ኤሌክትሪክ ደረጃውን ያሻሻለበትን ድል አስመዝግቧል፡፡

08:30 ላይ በቅዱስ ጊዮርጊስ እና አዲስ አበባ ከተማ መካከል የተደረገው ጨዋታ ሁለቱም እስከ 5ኛ ያለውን ደረጃ ይዘው ለማጠናቀቅ ወሳኝ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ትኩረት አግኝቶ ነበር፡፡ በስታድየሙ የጥላ ፎቅም በርካታ ቁጥር ያለው ተመልካች ተከታትሎታል፡፡

ጨዋታው ያለ ግብ በአቻ ውጤት የተጠናቀቀ ሲሆን በሁለተኛው አጋማሽ ቅዱስ ጊዎርጊሶች ግብ ሊሆኑ የሚችሉ ያለቀላቸው የግብ እድሎች አግኝተው ሳይጠቀሙባቸው ቀርተዋል፡፡

ከጨዋታው ፍፃሜ በኋላ ከረጅም ጊዜ የእግር ህመሟ ለማገገም ከፍተኛ የህክምና ወጪ የሚያስፈልጋት የኢትዮጵያ ቡናዋ አሰልጣኝ እየሩሳሌም ነጋሽ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር የ50,000 ብር ድጋፍ ተደርጎላታል፡፡

ቀጥሎ የተደረገው የመከላከያ እና የኢትዮ-ኤሌክትሪክ ጨዋታ በኤሌክትሪክ 1-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ በዘንድሮው የውድድር ዘመን የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ከፍተኛ መሻሻል ማሳየት ከቻሉ ክለቦች አንዱ የሆነው ኤሌክትሪክ ነጥቡን — በማድረስ 3ኛ ደረጃን መያዝ ችሏል፡፡

የሊጉ ቀጣይ መርሀግብሮች ነገ ከታች በተገለፁ መርሀ ግብሮች ይቀጥላሉ፡-



Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *