ፋሲል ከተማ እና አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ተለያዩ

የፋሲል ከተማው አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ከክለቡ ለመልቀቅ በደብዳቤ መጠየቃቸውን ተከትሎ የክለቁ ቦርድ ጥያቄያቸውን ተቀብሎ ከአጼዎቹ ጋር ተያየይተዋል፡፡

በ25ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አአ ስታድየም ላይ ፋሲል ከተማ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 3-1 ከተረታ በኋላ አሰልጣኝ ዘማርያም ከክለቡ አሰልጣኝነታቸው በገዛ ፍቃዳቸው መልቀቃቸውን ገልፀው የነበረ ቢሆንም በማግስቱ ለሶከር ኢትዮጵያ በሰጡት አስተያየት ለአንድ ወር ህክምና ወደ ታይላንድ እንደሚጓዙ ገልጸው ስራቸውን ለመልቀቅ ግን እንዳልወሰኑ ገልጸው ነበር፡፡ ሆኖም ከሰአታት በኋላ ለክለቡ ያስገቡት መልቀቂያ ተቀባይነት አግኝቶ ከክለቡ ጋር መለያየታቸው እርግጥ ሆኗል፡፡

ፋሲል ከተማ የዘማርያም ረዳት የነበሩት ምንተስኖት ጌጡን እስከ ውድድር አመቱ መጨረሻ ክለቡን እንዲመሩ ሲሾም የቀድሞው የዳሽን ቢራ አሰልጣኝ ተገኝ እቁባይ በረዳትነት እንዲሰሩ ተወስኗል፡፡ የክለቡ ቦርደድ በቀጣይ የውድድር ዘመን ክለቡን እንዲመሩ በእጩነት አሰልጣኞችን መያዙ ሲታወቅ አስራት ኃይሌ ፣ ሰውነት ቢሻው ፣ ውበቱ አባተ እና መኮንን ሃብተዮሀንስ ለቀጣይ አሰልጣኝነት የታሰቡ ናቸው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *