ፌዴሬሽኑ እነ አርቢትር ይርጋለም ላይ የ6 ወራት ቅጣት አሳለፈ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ረቡእ የተደረገውን የሐረር ሲቲ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጨዋታ ተከትሎ የሀረር ሲቲ እግርኳስ ክለብ ያቀረበውን ቅሬታ ተከትሎ ጨዋታውን የመሩት ዳኞች ላይ ቅጣት አስተላልፏል፡፡

ለቅጣቱ እና ለሀረር ሲቲ ቅሬታ መነሻ የሆነው ጨዋታው 1-1 በነበረበት ሰአት ዋና ዳኛ ይርጋለም ለሐረር ሲቲ ሊሰጥ የሚገባውን የፍፁም ቅጣት ምት ሆን ብለው ከልክለዋል በሚል ነው፡፡

ፌዴሬሽኑ በውሳኔው መሰረት የእለቱ ዋና ዳኛ ይርጋለም ወልደ ጊዮርጊስን ለ6 ወራት ከማንኛውም የእርግርኳስ ውድድሮች ዳኝነት ሲያግድ ረዳት ዳኛው ቦጋለ አበራን ደግሞ የ3 ወራት ቅጣት አስተላልፎባቸዋል፡፡ የጨዋታው ኮሚሽነር የነበሩት አርቢትር ታረቀኝ ለማ ደግሞ የእለቱን ሁኔታ በትክክል ሪፖርት ባለማድረጋቸው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡

የሐረር ሲቲው አሰልጣኝ ኃይማኖት ግርማ ከጨዋታው በኋላ በሰጡት አስተያየት ‹‹ጨዋታው ሳይካሄድ በፊት ፕሪ ማች ሚቲንግ ላይ የተመደቡት አራቱም ዳኞች ከአዲስ አበባ መሆናቸውን ተናግረን እንዲስተካከልም አሳስበን ነበር፡፡ ነገር ግን ተገቢውን ምላሽ አላገኘንም ፡፡ በጨዋታው ዳኞቹ የተጋጣሚያችን 12ኛ ተጫዋች ነበሩ፡፡ ›› በማለት በዳኝነቱ ዙርያ ምሬታቸውን ገልፀው ነበር፡፡

ፌዴሬሽኑ በእነ አርቢትር ይርጋለም ላይ ያሳለፈው ቅጣት በ1 ወር ውስጥ 2ኛው ነው፡፡ ከዚህ በፊት አርቢትር አሸብር ሰቦቃ ዳሽን ቢራ ላይ አላግባብ የፍፁም ቅጣት ምት አሰጥተዋል በሚል 6 ወራት መታገዳቸው ይታወሳል፡፡

{jcomments on}

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *