ኢትዮጵያ ከ ዛምቢያ አዲስ አበባ ላይ ይጫወታሉ

ለ2017 የአፍሪካ ዋንጫ እና የ2016 የቻን ውድድር ማክሰኞ ዝግጅት የጀመረው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከዛምቢያ ጋር የሚያደርገው የዝግጅት ጨዋታ አዲስ አበባ ስታድየም ላይ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

የዛምቢያ ብሄራዊ ቡድን ከነገ በስቲያ (አርብ) አዲስ አበባ የሚገባ ሲሆን እሁድ ግንቦት 30/2007 በአዲስ አበባ ስታድየም ጨዋታው ይደረጋል፡፡

የብሄራዊ ቡድኑ የቡድን መሪ አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ ባለፈው ሰኞ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የዛምቢያ ብሄራዊ ቡድን ወደ አዲስ አበባ እንዲመጣ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን የ10 ተጫዋቾቹን የትኬት ወጪ እደቻለ መግለፃቸው የሚታወስ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ከ ዛምቢያ - በ2013 የአፍሪካ ዋንጫ
ኢትዮጵያ ከ ዛምቢያ – በ2013 የአፍሪካ ዋንጫ
ያጋሩ