ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ :  መሪዎች ወልዋሎ  እና መቀለ ከተማ ወደ አሸናፊነት ተመልሰዋል

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 21ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ሰኞ እና ዛሬ በአዲስ አበባ እና ክልል ከተሞች ሲደረጉ በደረጃ ሰንጠረዡ አናት የሚገኙት ወልዋሎ ፣ መቀለ እና ሽረ እንዳስላሴ ተጋጣሚዎቻቸውን ማሸነፍ ችለዋል፡፡

አዲግራት ላይ አራዳ ክፍለከተማን ያስተናገደው ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲ 3-0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ድሬዳዋ ከተማን ለቆ ወልዋሎን በውድድር አመቱ አጋማሽ የተቀላቀለው አሳሪ አልማህዲ በ26 እና 90ኛ ደቂቃዎች ሁለት ጎሎች ሲያስቆጥር መኩሪያ ደሱ ቀሪዋን ግብ በ26ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል፡፡

ሁለቱን የትግራይ ቡድን ያገናኘውና ከፍተኛ ፉክክር ያስተናገደው የመቀለ ከተማ እና አክሱም ከተማ ጨዋታ መቀለ ዩንቨርሲቲ ስታድየም ላይ ተካሂዶ መቀለ 2-1 ማሸነፍ ችሏል፡፡ ዜናው ፈረደ በ4ኛው ደቂቃ መቀለን በዳሚ ቢያደርግም አክሱም ከተማ በመጀመርያው አጋማሽ መጠናቀቂያ ሚፍታ አወል ባስቆጠረው ግብ አቻ መቶን ችለዋል፡፡ ጨዋታው በአቻ ውጤት ይጠናቀቃል ተብሎ ሲጠበቅ በ85ኛው ደቂቃ ላይ አማኑኤል ገ/ሚካኤል መቀለ ከተማን ወደ ድል የመራች ጎል አስቆጥለሯል፡፡

ወደ ሰበታ ያቀናው ሽረ እንዳስላሴ በአስደናቂ ጉዞው ቀጥሎ ሰበታ ከተማን 1-0 አሸንፎ ተመልሷል፡፡ የሽረን ወሳኝ የድል ጎል ጨዋታው በተጀመረ ገና በ2 ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ብሩክ ነው፡፡ ዘንድሮ ከፍተኛ ሊጉን የተቀላቀለው ሽረ አስደናቂ ጉዞ በማድረግ 3ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡

መድን ሜዳ ላይ ባሀህርዳር ከተማን ያስተናገደው ኢትዮጵያ መድን ያለ ግብ አቻ ተለያይቷል፡፡ በሁለተኛው ዙር የተዳከመው ባህርዳር ደረጃው ወደ 4ኛ ወርዶ ወደ ፕሪምየር ሊግ የመግባት ተስፋውን አጨልሟል፡፡

በሌሎች የትላንት ጨዋታወች ወሎ ላይ ወሎ ኮምቦልቻ በቃለፍቅር መስፍን የመጀመርያ አጋማሽ ጎል ኢትዮጵያ ውሀ ስፖርትን 1-0 ሲረታ ቡራዩ ከተማ ሰሜንሸዋ ደብረብርሀንን አስተናግዶ በተመሳሳይ 1-0 አሸንፏል፡፡ ሱሉልታ ላይ ሱሉልታ ከተማ ከ ለገጣፎ ለገዳዲ ያለ ግበብ አቻ የተለያዩበት ሌላው የትላንት መርሀግብር ነበር፡፡

በትላንትናው እለት ኦሜድላ ሜዳ ላይ ሊካሄድ የነበረው የአዲስ አበባ ፖሊስ እና አማራ ውሀ ስራ ጨዋታ በጣለው ዝናብ ምክንያት ሜዳው በመጨቅየቱ ለዛሬ ተሸጋግሯል፡፡ በዚህም ዛሬ 5:00 ላይ በአዲስ አበባ ስታድየም ጨዋታው ተደርጎ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተፈፅሟል፡፡

 

የደረጃ ሰንጠረዥ

1 Comment

Leave a Reply