ቻምፒየንስ ሊግ ፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ማሜሎዲ ሰንዳውንስን በሚቀጥለው ቅዳሜ ይገጥማል

የ2017 ቶታል ካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ከሳምንት በኃላ በተለያዩ የአፍሪካ ከተሞች በሚደረጉ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታዎች ይጀመራል፡፡ በውድድሩ ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያው ተወካይ ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከወቅቱ የአፍሪካ ቻምፒዮን ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ጋር ፕሪቶሪያ ላይ ያደርጋል፡፡

የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ቅዳሜ ግንቦት 5 እንደሚደረግ ካፍ ያወጣው መርሃ-ግብር ያስረዳል፡፡ በ27ኛ ሳምንት የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ወደ ጅማ አቅንቶ ጅማ አባ ቡናን የሚገጥሙት ፈረሰኞቹ ከጅማ መልስ ወደ አህጉሪቱ ታላቅ ውድድር ፊታቸውን የሚያዞሩ ይሆናል፡፡ በምድብ ሶስት ሌላ ጨዋታ ኤኤስ ቪታ ክለብ ወደ ቱኒዝ አቅንቶ ኤስፔራንስ ደ ቱኒዝን አርብ ግንቦት 4 ይገጥማል፡፡

የምድቡ ሁለተኛ ጨዋታ በግንቦት ወር የሚካሄድ ሲሆን ፈረሰኞቹ በሜዳቸው ኤስፔራንስን ያስተናግዳሉ፡፡ ብራዚሎቹ ወደ ኮንጎ በማቅናት ቪታን የሚገጥሙበት ሎላኛው ጨዋታ ነው፡፡

የምድብ ጨዋታዎች የሚከናወኑባቸው ጊዜያት

የምድቡ መክፈቻ ጨዋታዎች

አርብ ግንቦት 4/ 2009

15፡00 – ኤስፔራንስ ደ ቱኒዝ ከ ኤኤስ ቪታ ክለብ

ቅዳሜ ግንቦት 5/2009

15፡00 – ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

የምድቡ ሁለተኛ ጨዋታዎች

ማክሰኞ ግንቦት 15/ ረቡዕ ግንቦት 16/2009

ኤኤስ ቪታ ክለብ ከ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኤስፔራንስ ደ ቱኒዝ

ምድቡ ሶስተኛ ጨዋታዎች

ከግንቦት 25-27/ 2009 ባሉት ቀናት

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኤኤስ ቪታ ክለብ

ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ከ ኤስፔራንስ ደ ቱኒዝ

ምድቡ አራተኛ ጨዋታዎች

ሰኔ 13-14/2009

ኤኤስ ቪታ ክለብ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

ኤስፔራንስ ደ ቱኒዝ ከ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ

የምድቡ አምስተኛ ጨዋታዎች

ከሰኔ 25-27/2009 ባሉት ቀናት

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ

ኤኤስ ቪታ ክለብ ከ ኤስፔራንስ ደ ቱኒዝ

የምድቡ ስድስተኛ ጨዋታዎች

ከሰኔ 30-ሐምሌ 2/2009 ባሉት ቀናት

ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ከ ኤኤስ ቪታ ክለብ

ኤስፔራንስ ደ ቱኒዝ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *