በሀድያ ሆሳዕና ላይ የተጣለው የ6 ነጥቦች ቅነሳ ተነሳ

ሀድያ ሆሳዕና በፌዴሬሽኑ የተጣለበት የ6 ነጥብ ቅነሳ ሲነሳለት በምትኩ 2 የሜዳ ጨዋታውን በዝግ ስታድየም እንዲያካሂድ ተወስኖበታል፡፡

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን ኮሚቴ ከ2 ሳምንት በፊት ባስተላለፈው ውሳኔ የከፍተኛ ሊጉ ክለብ የሀድያ ሆሳዕና ደጋፊዎች በተደጋጋሚ በፈጸሙት የዲሲፕሊን ጥሰት ከሰበሰበው ነጥብ ላይ 6 ነጥቦች እንዲቀነሱበት ውሳኔ ማስተላለፉ የሚታወስ ነው፡፡

ከቅጣት ውሳኔው በኋላ ሀድያ ሆሳዕና ይግባኝ የጠየቀ ሲሆን ጉዳዩን ያየው የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴም ቅጣቱን መሻሩ ታውቋል፡፡ በዚህም ሀድያ ሆሳዕና ከነበረው 30 ነጥብ ላይ የተቀነሰው 6 ነጥብ ተጨምሮለት ነጥቡን ወደ 36 በማድረስ ከመሪዎቹ ጅማ ከተማ እና ሀላባ ከተማ ጋር በነጥብ መስተካከል ችሏል፡፡

ሀድያ ሆሳዕና ነጥቡ ቢመለስለትም በምትኩ ሌላ ቅጣት ተጥሎበታል፡፡ በቀጣይ በአቢዮ አርሳሞ ስታድየም የሚያደርጋቸው ሁለት  ጨዋታዎችንም ያለ ደጋፊ በዝግ ስታድየም እንዲያካሂድ ተወስኖበታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *