ሉሲዎቹ በሜዳቸው ሲሸነፉ ከ20 አመት በታች ቡድኑ ከማጣርያው ውጪ ሆነ ፣ መከላከያ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፈ

›› ለሴኔጋሉ የአፍሪካ ከ20 አመት በታች ቻምፒዮንሺፕ ማጣርያ 1ኛው ዙር ደርሶ የነበረው የኢትዮጵ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ጉዞ በደቡብ አፍሪካ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ተገትቷል፡፡

አዲስ አበባ ላይ በተደረገው የመጀመርያ ጨዋታ 2-0 የተሸነፈው ብሄራዊ ቡድኑ በርካታ ለውጦችን አድርጎ እንዲሁም የብሄራዊ ቡድኑን ዋና አሰልጣኝ ይዞ ወደ ጆሃንስበርግ ቢያቀናም ከሽንፈት አልዳነም፡፡

ለደቡብ አፍሪካ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ብቸኛዋን ግብ ከመረብ ያሳረፈው ናላካኒፖ ንቱሊ በ40ኛው ደቂቀቃ በፍፁም ቅጣት ምት ነው፡፡ ደቡብ አፍሪካ የትላንትናውን ውጠት ተከትሎ በ3-0 ድምር ውጤት ወደ ቀጣዩ ዙር አልፋለች፡፡ በመጨረሻው የማጣርያ ዙርም የካሜሩን ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድንን ትገጥማለች፡፡

›› ለ2015ቱ የናሚቢያ የአፍሪካ ሴቶች ቻምፒዮንሺፕ የማጣርያ ጨዋታ የጋና ሴቶች ብሄራዊ ቡድንን ያስተናገደው የኢትዮጵ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ( ሉሲ ) በገዛ ሜዳው 2-0 ተሸንፎ የማለፍ ተስፋው አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል፡፡ ለጋና የድል ግቦቹን ሰሚራ ሱሌይማን እና ተቀይራ የገባችው ኤሊዛቤት ኮሊጃ አስቆጥረዋል፡፡ ከጨዋታው በኋላ የጋናው አሰልጣኝ የኢትዮጵያ ሴቶች ቡድን ከውጤት ይልቅ ተመልካች ለማዛናናት ወደ ሜዳ የገባ ይመስላል ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

የስዩም ከበደ ስብስብ በመልሱ ጨዋታ የ2-0 ሽንፈት የመቀልበስ ትልቅ ፈተና ይጠብቀዋል፡፡

›› ዘንድሮ በተጀመረው የሴካፋ ናይል ቤዚን ቻምፒዮንሺፕ እየተካፈለ የሚገኘው መከላከያ ትለንት የጅቡቲው ድሂክልን 2-1 አሸንፏል፡፡ የግብፁ አል-ማስሪ ከውድድሩ ራሱን ማግለሉን ተከትሎ በ3 ክለቦች መካካል በሚደረገው የምድብ ፉክክር አህሊ ሼንዲ እና መከላከያ ከወዲሁ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *