የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አዲስ አሰልጣኝ ሆነው ከወራት በፊት የተሸሙት አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ዝግጅት 29 ተጫዋቾችን መርጠዋል፡፡
በምርጫው ውስጥ አወት ገብረሚካኤል ፣ አብዱራህማን ሙባረክ እና አሜ መሀመድ ለመጀመርያ ጊዜ ጥሪ ሲቀርብላቸው ኡመድ ኡኩሪ እና ተስፋዬ በቀለ ከረጅም ጊዜ በኋላ ወደ ብሄራዊ ቡድን መመለስ ችለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የ2017 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታውን በመጪው ሰኔ 3 ወደ አክራ አቅንቶ ጋናን የሚገጥም ሲሆን ከዚህ ጨዋታ ቀደም ብሎ ግንቦት 26 ከዩጋንዳ ብሄራዊ ቡድን ጋር አዲስ አበባ ላይ የአቋም መፈተሸ ጨዋታ የሚያደር ይሆናል፡፡
የአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ 29 ተጫዋቾች ዝርዝር ይህንን ይመስላል፡-
ግብ ጠባቂዎች
ለአለም ብርሃኑ (ሲዳማ ቡና) ፣ ጀማል ጣሰው (ጅማ አባ ቡና) ፣ አቤል ማሞ (መከላከያ) ፣ ተክለማርም ሻንቆ (አአ ከተማ)
ተከላካዮች
አስቻለው ታመነ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ስዩም ተስፋዬ (ደደቢት) ፣ አብዱልከሪም መሀመድ (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ አህመድ ረሺድ (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ ተስፋዬ በቀለ (አዳማ ከተማ) ፣ አንተነህ ተስፋዬ (ሲዳማ ቡና) ፣ አወት ገብረሚካኤል (ኢትዮ ኤሌክትሪክ) ፣ አዲሱ ተስፋዬ (መከላከያ) ፣ ሙጂብ ቃሲም (አዳማ ከተማ)
አማካዮች
ናትናኤል ዘለቀ (ቅዱስ ጊርጊስ) ፣ ብሩክ ቃልቦሬ (አዳማ ከተማ) ፣ ምንተስኖት አዳነ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ኤፍሬም አሻሞ (ደደቢት) ፣ ሽመክት ጉግሳ (ደደቢት) ፣ ጋቶች ፓኖም (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ ታደለ መንገሻ (አርባምንጭ ከተማ) ፣ ሙሉአለም መስፍን (ሲዳማ ቡና) ፣ ጋዲሳ መብራቴ (ሀዋሳ ከተማ) ፣ ሽመልስ በቀለ (ፔትሮጄት/ግብፅ)
አጥቂዎች
ጌታነህ ከበደ (ደደቢት) ፣ ሳላዲን ሰኢድ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ኡመድ ኡኩሪ (ኤንታግ ኤልሀርቢ/ግብፅ) ፣ አብዱራህማን ሙባረክ (ፋሲል ከተማ) ፣ አሜ መሀመድ (ጅማ አባ ቡና) ፣ አዲስ ግደይ (ሲዳማ ቡና)