ቻምፒየንስ ሊግ | ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚጓዙ 18 ተጫዋቾች ታውቀዋል 

ቅዱስ ጊዮርጊስ የቶታል ካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ የመጀመርያውን የምድብ ጨዋታ ለማድረግ በነገው እለት ወደ ደቡብ አፍሪካ ፕሪቶርያ ያቀናል፡፡ 

የአሰልጣኝ ማርት ኑይ ስብስብ በዛሬው እለት የመጨረሻ ልምምዱን የሰራ ሲሆን ማሜሎዲ ሰንዳውስን በሚገጥምበት ጨዋታ የሚጠቀምባቸው 18 ተጫዋቾችንም ለይቷል፡፡

በዝርዝሩ ውስጥ ካልተካተቱት መካከል ክለቡ ወደ ምድብ ድልድሉ እንዲገባ ከፍተኛውን ሚና የተወጡት ሳላዲን ሰኢድ እና ምንተስኖት አዳነ በቅጣት አብረው የማይጓዙ ሲሆን ጉዳት ላ የሚገኘው በኃይሉ አሰፋም ከ18 ተጫዋቾች ዝርዝር ውጪ ሆኗል፡፡ በቅርቡ ከጉዳት ያገገሙት ምንያህል ተሾመ እና ራምኬል ሎክ ደግሞ በስብስቡ ውስጥ ተካተዋል፡፡

ወደ ፕሪቶርያ የሚቀናው ቡድን ስብስብ ይህንን ይመስላል፡-

ግብ ጠባቂዎች

ሮበርት ኦዶንካራ ፣ ዘሪሁን ታደለ

ተከላካዮች

ደጉ ደበበ ፣ ሳላዲን በርጊቾ ፣ አስቻለው ታመነ ፣ አበባው ቡታቆ ፣ መሀሪ መና ፣ ፍሬዘር ካሳ ፣

 አማካዮች 

ተስፋዬ አለባቸው ፣ አብዱልከሪም ኒኪማ ፣ ናትናኤል ዘለቀ ፣ ያስር ሙገርዋ ፣ ምንያህል ተሾመ

አጥቂዎች

አቡበከር ሳኒ ፣ አዳነ ግርማ ፣ ፕሪንስ ሰቨሪንሆ ፣ ብሩኖ ኮኔ ፣ ራምኬል ሎክ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *