አዳነ ግርማ ለብሔራዊ ቡድን ስለቀረበለት ጥሪ ይናገራል

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በቀጣዩ ወር የአመቱን የመጀመርያ የነጥብ ጨዋታ ያደርጋል፡፡ አዲሱ የዋልያዎቹ አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለም 29 ተጫዋቾችን መርጠዋል፡፡ አሰልጣኙ በስብስባቸው አንጋፋው አጥቂ አዳነ ግርማን ለማካተት ጥሪ ለተጫዋቹ አቅርበውለት እንደነበረም ተሰምቷል፡፡

በጉዳዩ ዙርያ ለሶከር ኢትዮጵያ አስተያየቱን የሰጠው አዳነ ግርማ አሰልጣኝ አሸናፊ ጥሪ አቅርበውለት እንደነበር ገልጿል፡፡ ” በርግጥ አሁን ያለኝ ወቅታዊ አቋም የሚያጫውተኝ ቢሆንም በዚህ ሶስት አመት ውስጥ ራሴን ከብሔራዊ ቡድን አግልያለሁ። ከብሔራዊ ቡድን ካገለልኩ ጀምሮ ብዙ አሰልጣኞች እንድመለስ ጠይቀውኛል ፤ አሁንም አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ እንድጫወት ጠይቆኛል፡፡ በዚህም አመሰግነዋለው። እንደሚታወቀው ለሀገሬ ከ10 አመት በላይ አቅሜ በቻለ ነገር ሁሉ አገልግያለው፡፡ በዚህም በጣም ደስተኛ ነኝ። አሁን ክለቤ ላይ ትኩረት ማድረግ ስለምፈልግ እንጂ አቅሜ ሳይችል ቀርቶ አይደለም ራሴን ከብሔራዊ ቡድን ያገለልኩት። ” ሲል አዳነ ተናግሯል፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊሱ አጥቂ የአሰልጣኙ ምርጫ ላይ በሰጠው አስተያየት የአሸናፊን ምርጫ እንደሚያከብር ጠቁሟል፡፡ ” አሰልጣኙ የራሱ አካሄድ አለው፡፡ በብዛት በቡድናቸው ውስጥ ጥሩ የሚንቀሳቀሱ ሀገር ውስጥ አሉ የሚባሉ ተጨዋቾች ተመርጠዋል። ሆኖም መጠራት እየተገባቸው ያልተመረጡ አሉ፡፡ የአሰልጣኙን ስራ የማከብር ቢሆንም ወደ ፊት እያየ ይጨምራል ብዬ አስባለው። አሁን ለራሱ አጨዋወት ታክቲክ ይመጥናሉ ብሎ ያመነበትን መርጧል፡፡ እንግዲህ ስራውን ለእርሱ መተው ነው። በዚህ አጋጣሚ መልካም እድል እመኝለታለሁ።

አዳነ ግርማ በ2006 ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ ካገለለ ወዲህ ዋልያዎቹ 3 አሰልጣኞችን ቀያይረዋል፡፡ ደጉ ደበበ እና አይናለም ኃይለም የአዳነን ፈለግ ተከትለው ራሳቸውን ከብሔራዊ ቡድን አግልለዋል፡፡ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ፣ የአለም ዋንጫ ማጣርያ እና የቻን ውድድሮች ላይ ተሳትፋም መልካም ውጤቶችን አላስመዘገበችም፡፡ አዳነም ባገለለባቸው አመታት ያለው ብሔራዊ ቡድን አለመረጋጋት እንደሚታይበት ያምናል፡፡

” ብሔራዊ ቡድኑ ብዙ አሰልጣኝ ነው የተፈራረቀበት፡፡ እኔ እንደ ብሔራዊ ቡድን ሳስበው በሌላው አለም አንድ አሰልጣኝ ሁለት አመት እና ከዛ በላይ ጊዜ ይሰጠዋል። እኛ ሀገር የስድስት ወር እና የአንድ አመት ውል እየሰጠህ  እንዴት ነው የሚሆነው? ይህ አይነት አሰራር ሊቀር ይገባል፡፡ ኢትዮጵያም የሌሎች ሀገሮችን ተመኩሮ መውሰድ አለባት እላለው። ” ሲል በብሄራዊ ቡድኑ ዙርያ ያለውን ሀሳብ ቋጭቷል፡፡

በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ አሳሳቢ ከሆኑት ጉዳዮች አንዱ የሆነው የተጫዋቾችን ክብር የሚነካ ዘለፋ ነው፡፡ ዘንድሮ በተለያዩ ተጫዋቾች ላይ ይህ ተግባር ተፈፅሞ በክለቦች ላይ ቅጣቶች መጣሉም የሚታወስ ነው፡፡ ከጉዳዩ ሰለባዎች አንዱ የሆነው አዳነ ግርማ ይህ ተግባር ሊወገድ እንደሚገባ ተናግሮ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር የነበረውን ቆይታ ቋጭቷል፡፡

” እንደ ደጋፊ ሳስበው ስታድየም የሚመጡት ሊዝናኑ እና የሚወዱት ቡድናቸውን ሊደግፉ እንጂ የተቃራኒን ቡድን እና ተጨዋች ለመሳደብ አይደለም። እስከ መጨረሻው ደቂቃ ድረስ ቡድንህን እና ቡድንህን ብቻ ደግፈህ መውጣት ነው ያለብህ። ይህን መልዕክት የማስተላልፈው ለዚህ ቡድን ለዛ ብዬ አይደለም ፤ ለሁለም ቡድን ደጋፊዎች ነው። ቡድናቸውን ደግፈው ቡድናቸው ተዝናንተው በሚመዘገበው ውጤት ቢያሸንፍም ተደስተው ቢሸነፍም ተከፍተው ቡድናቸው ላይ መስተካከል ያለበትን ነገር አግባብ ባለው መንገድ ተናግሮ መሄድ ነው እንጂ የተቃራኒ ቡድን ተጨዋች መስደብ ተገቢ አይደለም። አሁን የስፖርት ቤተሰቡ ወደ ሜዳ መምጣቱ ትልቅ ነገር ነው። ይህን ህዝብ በስታድየም ለማስቀረት አላስፈላጊ ነገሮችን መቅረፍ አለብን ብዬ አስባለሁ፡፡ “

9 Comments

 1. እድሜና ጤና ለምንጊዜም ምርጥ አሰልጣኝ ጋሽ ሰውነት ቢሻው ታሪክ ሰራልን ሁሉም የእርሱ ውጤት ነው።

 2. አዳነ ግርማ ከሌሎቹ ዋልያዎች ጋር ሆኖ ከወሳኞቹ ጎሎች አንዱን አግብቶ (በመጨረሻው ማጣሪያ ጨዋታ ላይ )ሀገሩን ለአፍሪካ ዋንጫ አድርሷል በአፍሪካ ዋንጫም በወቅቱ የአፍሪካን ዋንጫን አንስቶ በነበረው ቡድን ላይ ጎል አግብቷል – ጉዳት እስኪ ገጥመው ድረስ መሀል ሜዳውን በመቆጣጠር ተቀይሮ እስኪወጣ ድረስ የቡረኪና ፋሶ ብሔራዊ ቡድን አንድ ጎል ማግባት አይደለም በጨዋታም አልበለጠም -ይህን ሁሉ በሙያዉ በፈጣሪ እርዳታ ለሀገሩ ስላደረገው ነገር ማመስገን አለብን፡፡

 3. desta
  ኣዳነስ እሺ ቢያንስ 1 ጎል ኣለው …ደጉ እና ኣይንኣለም ያን ያህል ለውጥ ኣምጪዎች ነበሩ እያልክ ነው ..

 4. Alex ስለማታውቀውን ባትዘባረቅና የኢትዮጵያ እግር ኳስን ለሚከታተሉት ምናለበት? ውለታን መርሳት ለሀበሻ ባህሪው ነውና ላይፈረድብህ ይችላል። የዋልያ ስምና አርማ እንዲጋነንና ለCHAN ለአፍሪካ ዋንጫና የአለም ዋንጫ በራፍ ካደረሱንና ታሪክ ካስመዘገቡት መሃል ሁለቱ አይናለምና ደጉ ይገኛሉ።

  አዳነን በተመለከተ በ10 ዓመት የ ብ/ቡድን ቆይታው እንደተናገረው ሀገሩን በሚገባው አገልግሏል። በስተመጨረሻ ከMariano Barreto ጋር ተጋጭቶ ከቡድኑ ተሸኘ። ከቡድኑ መባረርና በደጋፊዎች መሰደብ አይገባውም ነበር። አዳነ ምንም እዳ የለበትም መመለስ አለመፈለጉም አልገረመኝም።

 5. ኣዳነም ሆነ ሌሎች ኖሩም ኣልኖሩ ቡድኑ ላይ የሚያመጡት ምንም ለውጥ ኣይኖርም በተለይ ደጉ እና እይናለም ክመጀመርያው መመረጣቸው እራሱ ተኣምር ነው
  ይልቅ ጥያቄው /እኔ ያልገባኝ ልብሄራዊ ቡድን ኣልጫውትም ማለት ይቻላል እንዴ ? ኣገርን ማገልገል ግዴታ ጭምር ኣይደለም እንዴ እስኪ ኣስረዱኝ…

  1. እባክህ ኣትርሳ እንጂ በደጉ እና ኣይናአለም ዘመን ነው ኣፍሪካ ዋንጫ ያየነው

   1. በደጉና በአይናለም ጊዜ ምንም ያየነው ነገር የለም የሰውነትም እራሱ ውጤት በድል የተገኘ ውጤት ነው አፍሪካ ዋንጫ የገባንበትን የሱዳንን ማንሳት ይቻላል ወይም የደቡብ አፍሪካን ሰውነትስ ቢሆን ዛሬ ላይ ብዙ ክለብ እየጠየቀው የማያሰለጥንበት ምክንያት ያችን ክብር እንዳያጣ ስለሚፈራ ነው ማለትም በብቃቱ ስለማይተማመን የአዳነን ነገር ተወው ባወራው አያልቅም ኢሄ ጥርብ ፋራ ከደጋፊ ጋር እልህ የሚጋባ

Leave a Reply