የታሪካዊ ፎቶዎች ኤግዚቢሽን በወሩ መጨረሻ ይካሄዳል

በቀደሙ አመታት የተነሱ የእግርኳስ ፎቶዎች ስብስብ በዚህ ወር መጨረሻ እንደሚካሄድ የፕሮግራሙ አዘጋጅ አንጋፋው የስፖርት ጋዜጠኛ ታሪኬ ቀጭኔ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጿል፡፡

ከግንቦት 25-27 ባሉት ሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቀርበውን ይህ ፕሮግራም አዲስ አበባ ስታድየም አጠገብ በሚገኘው ‘ ትንሿ ስታድየም ‘ ይካሄዳል፡፡ ይህን ኤግዚቢሽን ለማዘጋጀት ያለፉትን ወራት ሲሰራ እንደቆየ የገለጸው ጋዜጠኛ ታሪኬ የኤግዚቢሽኑ አላማ ቂርቆስ እና ለገሀር አካባቢ ለኢትዮጵያ ያፈራቸው ታላላቅ እና የሀገር ባለውለታ ስፖርተኞችን ከመዘከር በተጨማሪ በአጠቃላይ በቀደሙት አመታት የነበረውን የስፖርት እንቅስቃሴ እና ስፖርተኞችን የሚያሳዩ ምስሎችም ለእይታ እንደሚቀርቡ ገልጿል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *