ኮንፌድሬሽን ዋንጫ | ሱፐርስፖርት ዩናይትድ ከሆሮያ አቻ ተለያይተዋል

የካፍ ቶታል ኮንፌድሬሽን ዋንጫ የምድብ ጨዋታ አርብ ምሽት ፕሪቶሪያ ላይ በተደረገ አንድ ጨዋታ ሲጀመር ሱፐርስፖርት ዩናይትድ በሜዳው ከሆሮያ ጋር 2-2 ተለያይቷል፡፡

በምድብ መ ብቸኛ ጨዋታ የነበረው የሁለቱ ክለቦች ግጥሚያ ማራኪ ግቦች ቢታዩበትም ባለሜዳዎቹ የወረደ አቋም አሳይተዋል፡፡ ከሜዳው ውጪ ግቦችን ማስቆጠር ለማይሳነው የጊኒው ክለብም ውጤቱ መልካም ሆኖ አልፏል፡፡ የሆሮያ የቡድን አባላት ወደ ሉካስ ማስተርፒስስ ሞርፒ ስታዲየም ለመሄድ 45 ደቂቃዎች በሆቴላቸው መታገስ ነበረባቸው፡፡ የኮናክሬው ሃያል ክለብ በሱፐርስፖርት ዩናይትድ የደረሰበትን አግባብ ያልሆነ ስራ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ካሜሩናዊው ፍራንሲስ ዲፒታ ሆሮያን በ34ኛው ደቂቃ መሪ ሲያደርግ ኪገን ሪቲቼ በግሩም ሁኔታ ያስቆጠራት የቅጣት ምት ግብ ለእረፍት ቡድኖቹ በአቻ ውጤት ወደ መልበሻ ክፍል እንዲያመሩ አስችሏል፡፡ ጋናዊው ሰቤ ባፎር ኬዬ ሆሮያን ዳግም መሪ ሲያደርግ በሁለተኛው አጋማሽ ተቀይሮ ወደ ሜዳ የገባው ቱሶ ፓላ የአቻነቷን ግብ ለደቡብ አፍሪካው ክለብ አስቆጥሯል፡፡

የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ጨዋታዎች ዛሬ እና ነገ ሲቀጥሉ ሶስት ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ፡፡ ፉስ ራባት በሜዳው የዩጋንዳ አዛም ፕሪምየር ሊግ ቻምፒዮነ መሆኑን ከሳምንት በፊት ዳግም ያረጋገጠው ኬሲሲኤን በምድብ ሀ ሲያስተናግድ በምድብ ለ ሴፋክሲየን ምባባኔ ስዋሎስን እንዲሁም በምድብ ሐ ዜስኮ ዩናይትድ ስሞሃን የሚያስተናግድብት ጨዋታ የዛሬ መርሃ ግብሮች ናቸው፡፡

 

የአርብ ውጤት

ሱፐርስፖርት ዩናይትድ 2-2 ሆሮያ

የቅዳሜ ጨዋታዎች

ፋት ዩኒየን ስፖርት ከ ካምፓላ ሲቲ ካውንስል ኦቶሪቲ

ሴኤፍ ሴፋክሲየን ከ ምባባኔ ስዋሎስ

ዜስኮ ዩናይትድ ከ ስሞሃ

የእሁድ ጨዋታዎች

ክለብ አፍሪኬን ቱኒዝ ከ ሪቨርስ ዩናይትድ

ፕላቲኒየምስ ስታርስ ከ ሞሊዲያ ክለብ ዲ አልጀር

ክለብ ሬክሬቲቮ ዴስፖርቲቪ ዱ ሊቦሎ ከ አል ሂላል ኦባያድ

ቲፒ ማዜምቤ ከ ሲኤፍ ሞናና

Leave a Reply