ቻምፒየንስ ሊግ | ዛናኮ አል አህሊን ነጥብ አስጥሏል

በቻምፒየንስ ሊግ የምድብ መክፈቻ የመጨረሻ ጨዋታ የ8 ግዜ የአፍሪካ ቻምፒዮኑ አል አህሊ በሜዳው እና ደጋፊው ፊት ከዛምቢያው ዛናኮ ጋር ያለግብ አቻ ተለያይቷል፡፡ በሙከራ የተሻሉ የነበሩት አህሊዎች ግብ ማስቆጠር የሚችሉባቸውን አጋጣሚዎች በሙሉ አምክነዋል፡፡

በመጀመሪያው አጋማሽ አህሊ በአጥቂው ሱሌማና ኩሊባሊ አማካይነት ሁለት ኢላማቸውን ያልጠበቁ የግብ ሙከራዎች ሲያደርግ በአንፃሩ የዛምቢያው ክለብ ሙከራ ለማድረግ ሲቸገር ተስተውሏል፡፡ የዛናኮ ግብ ጠባቂ ቶስተር ንሳባታም የአህሊ ሙከራዎች በማምከን ስራ በዝቶበት አምሽቷል፡፡ ንሳባታ በሁለተኛው አጋማሽ የአምበሉን ሆሳም ጋሊ የግንባር ኳስ እንዲሁም በጨዋታዎቹ የመጨረሻ ደቂቃ ኩሊባሊ የሞከረውን ሙከራ በማውጣት ለዛናኮ አንድ ነጥብ ማግኘት ወሳኝ ነበር፡፡ አምና በተመሳሳይ ውድድር ከምድብ ማለፍ ላልቻለው አል አህሊ ውጤቱ መልካም የሚባል አይደለም፡፡

የኢትዮጵያው ተወካይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከማሜሎዲ ሰንዳውንስ ያለግብ አቻ የተለያየበት እንዲሁም ዛናኮ በአሌክሳንደሪያ ያሳካው ነጥብ በመጀመሪያ ዙር የተመዘገቡ አስገራሚ ውጤቶች ናቸው፡፡

የአንደኛ ዙር ውጤቶች

ምድብ ሀ

ኤቷል ደ ሳህል 5-0 ክለብ ፌሮቫያሪዮ ደ ቤይራ

አል ሂላል 1-1 ኤል ሜሪክ

 

ምድብ ለ

ዩኤስኤም አልጀር 3-0 አል አሃሊ ትሪፖሊ

ዛማሌክ 2-0 ካፕስ ዩናይትድ

 

ምድብ ሐ

ኤስፔራንስ ደ ቱኒዝ 3-1 ኤኤስ ቪታ ክለብ

ማሜሎዲ ሰንዳውንስ 0-0 ቅዱስ ጊዮርጊስ

 

ምድብ መ

ዋይዳድ አትሌቲክ ክለብ 2-0 ኮተን ስፖርት

አል አሃሊ 0-0 ዛናኮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *