የሌሴቶ ብሔራዊ ቡድን ባህርዳር ገብቷል

ሊክዌና (አዞዎቹ) በሚል ቅፅል ስም የሚታወቀው የሌሴቶ ብሔራዊ ቡድን ትናንት ባህርዳር ከተማ ደርሷል። የቡድኑ አሠልጣኝ ሲፌፌ ማቴቴ ከአንድ ተጫዋች ጉዳት በቀር የተሟላ ቡድን ይዘው ለጨዋታው የሚቀርቡ ይሆናል። ወጣቱ የሊኮፖ ክለብ አጥቂ ታፔሎ ታሌ በግንቦት ወር በተደረገው የደቡብ አፍሪካ ሃገራት ዋንጫ (ኮሳፋ) ላይ ሲጫወት ባጋጠመው ጉዳት ምክኒያት ከቡድኑ ጋር ወደ ኢትዮጵያ አልተጓዘም።

ቡድኑ ሙሉ በሙሉ በሃገር ውስጥ በሚጫወቱ ተጫዋቾች የተገነባ ሲሆን የሌሴቶ ፕሪምየር ሊግ የወቅቱ ሻምፒዮን ሊዮሊ 7 ተጫዋቾችን በማስመረጥ ይመራል። ባንቱ በ4 ተጫዋቾች ሁለተኛ ሲሆን ሊኮፖ እና ማትላማ ክለቦች እያንዳንዳቸው 3 ተጫዋቾችን በቡድኑ አካተዋል።

 

ሙሉ የሌሴቶ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ዝርዝር፡

 

ግብ ጠባቂዎች

ሞሃዉ ኩዌናኔ (ሊዮሊ)

ካናኔሎ ማክሆአኔ (ሊኮፖ)

 

ተከላካዮች

ንካው ሌሮትሆሊ (ማትላማ)

ታፔሎ ሞክሄህሌ (ባንቱ)

ጄሪ ካሜሌ (ሊዮሊ)

ታቢሶ ሞሃፒ (ባንቱ)

ቦካንግ ሞትሆአና (ሊኮፖ)

ሞቲኪ ሞሃሌ (ሌሮትሆሊ ፖሊቴክኒክ)

 

አማካዮች

ሶአኔሎ ኮኤትሌ (ሊዮሊ)

ሞትላሌፑላ ሞፎሎ (ሊዮሊ)

ቴቦሆ ሌክሆአ (ሊዮሊ)

ቡሺ ሞሌትሳኔ (ሊዮሊ)

ህሎምፖ ካላኬ (ባንቱ)

ማቡቲ ፖትሎዋኔ (ማትላማ)

ጄን ታባንትሶ (ማትላማ)

 

አጥቂዎች

ሊትሴፔ ማራቤ (ባንቱ)

ታቢሶ ብራውን (ኪክ4ላይፍ)

ንኮቶ ማሶአቢ (ሊዮሊ)

ቱሜሎ ኩትላንግ (ሊኮፖ)

ያጋሩ