የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ለሌላ ጊዜ ተሸጋገሩ

የኢትዮጵያ ዋንጫ (ጥሎ ማለፍ) ውድድር 1ኛ ዙር ጨዋታዎች በቀጣዩ ሳምንት እንዲካሄዱ መርሀግብር ወጥቶላቸው የነበረ ቢሆንም ላልታወቀ ጊዜ እንዲሸጋገሩ ተደርጓል፡፡

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ውድድሩን ለማራዘም ያስገደደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ዝግጅቱን በቀጣዩ ሳምንት የሚጀመር በመሆኑ ለዝግጅቱ በቂ ጊዜ እንዲያገኙ በማሰብ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ በፕሪምየር ሊጉ መርሀ ግብር ለውጥ ምክንያት የቀን ሸግሽግ መደረጉ የሚታወስ ሲሆን አሁን ላልታወቀ ጊዜ መሸጋገሩን ተከትሎ የዘንድሮው ውድድር የመካሄዱ ጉዳይ አጠራጣሪ እንዲሆን አድርጎታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *