አፍሪካ | ሴራሊዮን የአዲስ አሰልጣኝ ሹመት ይፋ አድርጋለች

የሴራሊዮን እግርኳስ ማህበር እና የሃገሪቱ የስፖርት ሚኒስቴር ዛሬ (ሐሙስ) አዲስ የብሄራዊ ቡድኑን አሰልጣኝ ይፋ አማድረጉን የሃገሪቱ የእግርኳስ ድህረ-ገፅ ፉትቦል ሴራሊዮን ዘግቧል፡፡ የቀድሞ የሴራሊዮን ኢንተርናሽናል ጆን ኬስተር አዲሱ ብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ሁነዋል፡፡ በምድብ ስደስት ከኢትዮጵያ ጋር የተደለደለችው ሴራሊዮን እንደዋሊያዎቹ ሁሉ ለረጅም ወራት ያለብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቆይታለች፡፡

የ46 ዓመቱ ኬስተር የተወለዱት ማንችስተር እንግሊዝ ሲሆን በተጫዋችነታቸው ለቸስተር ሲቲ እና ሽዌስቤሪ ታውን አማካይ ነበሩ፡፡ ሁለት ግዜ ለሃገራቸው መጫወት የቻሉት ቸስተር የጋናዊው አሰልጣን ሴላስ ቲቴ ምክትል በመሆን ብሀራዊ ቡድኑን አገልግለዋል፡፡ እንደFOOTBALLSIERRALEONE.NET ዘገባ ከሆነ የኬስተር ምክትል ሁነው የሚሰሩ አሰልጣኞች የቀድሞ የሴራሊዮን ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች የነበሩ ናቸው፡፡ ሴራሊዮንን በአምበልነት በ1994ቱ የቱኒዚያ እና 1996ቱ የደቡብ አፍሪካ የአፍሪካ ዋንጫዎች ላይ የመሩት አቡበከር ካማራ እና ጆን ሳማ የኬስተር ምክትል ሁነዋል፡፡

ኬስተር በ2016 የሴራሊዮን ክለብ የሆነውን ኤፍሲ ጆንሰንን ለኤፍኤ ዋንጫ ባለድልነው አብቅቷል፡፡ ሴራሊዮን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በምድብ ስድስት ኢትዮጵያ፣ ጋና እና ኬንያ ጋር ተደልድላለች፡፡ ሴራሊዮን የምድብ መክፈቻ ጨዋታዋን ከኬንያ ጋር ፍሪታውን ላይ ቅዳሜ ሰኔ 3 ታደርጋለች፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *