ክዌሲ አፒያ ለኢትዮጵያ ጨዋታ 30 ተጫዋቾችን ጠርተዋል

ጋና ሰኔ 4 ኩማሲ ላይ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጉዞዋን በምድብ መክፈቻ ጨዋታ ኢትዮጵያን በማስተናገድ ትጀምራለች፡፡ አሰልጣኝ ኩዌሲ አፒያም ለዝግጅት እንዲረዳቸው 30 ተጫዋቾችን ወደ ብሄራዊ ቡድኑ ጠርተዋል፡፡

ክዌሲ በጥቋቁር ከዋክብቶቹ ጊዜያዊ ስብስብ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ይታዩ የነበሩ አራት ነባር ተጫዋቾችን ሳይጠሩ መቅረታቸው አግራሞትን ፈጥሯል፡፡ በኒውካስል ዩናይትድ ድንቅ የውድድር ዘመን ያሳለፈው የመስመር አማካዩ ክሪስቲያን አትሱ ከቡድኑ ውጪ ሲሆን ግብ ጠባቂው ራዛክ ብሪማምን ሳይጠራ ቀርቷል፡፡ በጣሊያን የሚጫወተው ኢማኑኤል አግይማንግ ባዱ እና ሙባረክ ዋካሶ ሌሎች ጥሪ ያልተደረገላቸው ተጫዋቾች ናቸው፡፡

ክዌሲ በብድናቸው ጋናን ወደፊት ሊያራምዱ የሚችሉ ታዳጊ ተጫዋቾችን መያዝ እንደሚፈልጉ መናገራቸውን ተከትሎ የነበር ተጫዋቾች በቡድኑ ያላቸው ቆይታ አጠራጣሪ ነው፡፡ ነገር ግን በአፍሪካ ዋንጫው ተሳትፎ ያደረጉት የቡድኑ አምበል አሰሞሃ ጃን፣ ወንድማማቾቹ አንድሬ እና ጆርዳን አዩ፣ የመሃል ተከላካዩቹ ጆናታን ሜንሳ እና ጆን ቦይ፣ የመስመር ተከላካዩ ሃርሰን አፉል በቡድኑ ውስጥ ተካተዋል፡፡

በዲስፕሊን ግድፈት ምክንያት ከቡሄራዊ ቡድኑ የራቁት ኬቨን ፕሪንስ ቦአቴንግ እና ሱሊ አሊ ሙንታሪ አሁንም ወደ ብሄራዊ ቡድኑ የሚመልሳቸውን ጥሪ አላገኙም፡፡ በካታር በግሉ የተሻለ የውድድር ዘመን ያሳለፈው ራሺድ ሱማይላ እና አጥቂው አቡዱልመጅድ ዋሪስ ወደ ብሄራዊ ቡድኑ ከረጅም ቆይታ በኃላ ተመልሰዋል፡፡

ጋና ከኢትዮጵያ ጋር እሁድ ሰኔ 4 ኩማሲ በሚገኘው ባባ ያራ ስታዲየም ጨዋታው የምታደርግ ይሆናል፡፡ ቡድኑ ዝግጅትም ከግንቦት 21 ጀምሮ እንደሚያደርግ ታውቋል፡፡

ሙሉ ስብስብ

ግብ ጠባቂዎች

ሪቻርድ ኦፎሪ (ዋ ኦል ስታርስ)፣ አደም ክዋሬሲ (ብሮንድባይ/ዴንማርክ)፣ ፊሊክ አናን (አሻንቲ ኮቶኮ)፣ ጆሴፍ አዶ (አዱና ስታርስ)

ተከላካዮች

ሃርሰን አፉል (ኮሎምበስ ክሩ/ዩናይትድ ስቴትስ)፣ ዳንኤል አማርቴ (ሌስተር ሲቲ/እንግሊዝ)፣ ሉሞር አግቤንየኑ (1860 ሙኒክ/ጀርመን)፣ ዳንኤል ዳርካዋ (አዱና ስታርስ)፣ ጆን ቦይ (ሲቫስፖር/ቱርክ)፣ ራሺድ ሱማይላ (አል ጋርፋ/ካታር)፣ ኒኮላስ ኦፖኩ (በርከም ቸልሲ)፣ ጆናታን ሜንሳ (ኮሎምበስ ክሩ/ዩናይትድ ስቴትስ)፣ ጄሪ አካሚንኮ (ኢስኪሰርሂስፖር/ቱርክ)፣ ሳሙኤል ሳርፎ (ሊበርቲ ፕሮፌሽናል)

አማካዮች

መሃመድ አቡ (ኮሎምበስ ክሩ/ዩናይትድ ስቴትስ)፣ አፍሬ አኩዋ (ቶሪኖ/ጣሊያን)፣ አይዛክ ሳኪ (አሊያናስፖር/ቱርክ)፣ ቶማስ ፓርቴ (አትሌቲኮ ማድሪድ/ስፔን)፣ ኢቤኔዘር ኦፎሪ (ስቱትጋርት/ጀርመን)፣ ኪንግስሊ ሳርፎ (ሲሪስ/ስዊድን)፣ ዊንፉል ኮቢና(ሃርትስ ኦፍ ኦክ)፣ ያዎ የቦሃ (ኤፍሲ ትዌንቴ/ሆላንድ)፣ ጎድስዌይ ዶንዮ (ኖርድላንድ/ዴንማርክ)፣ አንድሬ አዩ (ዌስትሃም ዩናይትድ/እንግሊዝ)፣ ፍራንክ አቼምፖ (አንደርሌክት/ቤልጂየም)፣ ቶማስ አግዬፖ (ኤንኤሲ ብሬዳ/ሆላንድ)

አጥቂዎች

አሰሞሃ ጃን (ሻባብ አል አሃሊ ዱባይ/የተባበሩት የአረብ ኤምሬቶች)፣ ጆርዳን አዩ (ስዋንሲ ሲቲ/እንግሊዝ)፣ አብዱልማጂድ ዋሪስ (ሎርዮ/ፈረንሳይ)፣ ራፋኤል ዱዋሜና (ኤፍሲ ዙርክ፣ ስዊዘርላንድ)

Leave a Reply