ጋዜጠኛ ዘርአይ እያሱ ” ከሜዳ ውጪ” የተሰኘ መፅሀፍ አዘጋጀ

በተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን ለረጅም አመታት የስፖርት ፕሮግራሞችን በማቅረብ የሚታወቀው ጋዜጠኛ ዘርአይ እያሱ “ከሜዳ ውጭ” የተሰኘ አዲስ መፅሐፍ በቅርቡ ለገብያ ሊያቀርብ እንደሆነ ለሶከር ኢትዮዽያ ተናግሯል።

116 ገጾች ያሉት ይሀህ መፅሀፍ 45 ብር ዋጋ የተተመነለት ሲሆን በእግርኳሳች ሜዳ ላይ ከሚሰጥ ትኩረት በዘለለ ከሜዳ ውጪ ሊኖሩ ስለሚገባቸው ጉዳዮች እምብዛም ትኩረት አለመሰጠቱ መፅሀፉን ለማዘጋጀት እንዳነሳሳው ገልጿል፡፡ ” ብዙ ጊዜ ስለ እግር ኳስ ሲወራ ሜዳ ውስጥ ትኩረት የሚሰጣቸው በጨዋታ ጊዜ የቴክኒክ ፣ የታክቲክ አቀራረብ ፣ የጨዋታውን እንቅስቃሴ የመቃኘት  ላይ ማተከር እና ሌሎች ነገሮች ላይ ነው፡፡ ነገር  ግን ከሜዳ ውጭ ያሉ ብዙ ሌሎች ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ነገሮች አሉ፡፡ ለምሳሌ የአመራር ብቃት አሰልጣኞች ተጫዋቾቻቸውን እንዴት ነው የሚመሩት ፣ በተጨዋቾችና በአሰልጣኞች መካከል ያለው ግኑኝነት ፣ ለአምበልነት የምንሰጠው ግምት ምን ያህል ነው እና ሌሎች በርካታ ጠቀሜታ ያላቸው ነገሮች የተነሱ ሲሆን በአጠቃላይ በእግር ኳሱ ላይ ስኬታማ ለመሆን ሜዳ ውስጥ እና ከሜዳ ውጭ ያሉት ነገሮች ሊቀናጁ ይገባል፡፡ ”

ጋዜጤኛ ዘርአይ ለዚህ መፅሐፍ መሳካት በማረም ዳንኤል ገ/ማርያም  እና በፀሎት ልዑል ሰገድ ስነ ፁሁፋዊ ይዘቱን በማረም የዋኀላሸት ዘሪሁን እንደተባበሩት ገልጿል ።

1 Comment

  1. Zeray,
    It is Wonderful job
    keep it up and
    The other journalist should continue like this

Leave a Reply