በከፍተኛ ሊግ ተስተካካይ ጨዋታዎች ወልዋሎ እና መቀለ አሸንፈዋል

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 25ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ሐሙስ ግንቦት 17 ሳይካሄዱ የቀሩ ጨዋታዎች ሰኔ 2 ተካሂደው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና መቀለ ከተማ ከተከታዮቹ የራቁበትን ድል አስመዝግበዋል፡፡

ወደ አዲግራት ያመራው ባህርዳር ከተማ በመልካምና በማረ መልክ የአቀባበል ስነሰርዓት ተደርጎላቸዋል፡፡ የከተማው ከንቲባ አቶ ተስፋልደት ደስታ በአቀባበል ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙ ሲሆን የአዲግራት ዩንቨርስቲ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ፣ የአዲግራት ህዝብና ደጋፊ ማህበር ለባህር ዳር ከተማ ደጋፊዋችና ተጨዋቾች ከ20 ኪ.ሜ ርቀት ጀምሮ በማጀብ እና የዕራት ግብዣ በማድረግ መልካም የሚባል አቀባበል አድርጎላቸዋል፡፡

ወልዋሎ ጨዋታውን 2-0 በሆነ አሸናፊነት ሲያጠናቅቅ ኤፍሬም ጌታቸው በ35ኛው ደቂቃ ቀዳሚዋን መኩሪያ ደሱ ደግሞ በ83ኛው ደቂቃ ሁለተኛውን ጎል አስቆጥረዋል፡፡

መቀለ ከተማን ከወሎ ኮምቦልቻ ያገናኘው ጨዋታ በመቀለ 3-1 በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡ ጨዋታው በተጀመረ ከአንድ ደቂቃ ባነሰ ጊዜ አማኑኤል ገ/ሚካኤል ከያሬድ ከበደ የተሻገረትን ኳስ በማስቆጠር መቀለን ቀዳሚ ሲያደርግ በ22 ደቂቃ ላይ የወሎ ኮምቦልቻው ግብ ጠባቂ ሙሴ ዮሐንስ ሀዱሽ አውጣኝ ላይ በሰራው ጥፋት የተሰጠውን ፍፁም ቅጣት ምት ተጠቅሞ አማኑኤል ገ/ሚካኤል ለራሱና ለቡድኑ ሁለተኛውን ግብ አስቆጥሯል፡፡ በ25 ደቂቃ ፋሲል አስማማው ለወሎ ኮምበልቻ ግብ አስቆጥሮ 2-1 መሆን ቢችሉም በ44ኛው ደቂቃ ላይ ሀዱሽ አውጣኝ ሦስተኛውን ግብ አስቆጥሮ ጨዋታው 3-1 በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *