ኢትዮጵያ ከኬኒያ በባህርዳር ይካሄዳል

ኢትዮጵያ ከኬኒያ ጋር ለምታደረገው የቻን 2016 ማጣሪያ ጨዋታ በባህርዳር እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን አስታውቋል፡፡ የፌድሬሽኑ ፕሬዝዳንት ጁነዲ ባሻ በግል የትዊተር ገፃቸው ላይ እንዳሰፈሩት ከሆነ የኬኒያ እግርኳስ ፌድሬሽን በባህርዳር ስታዲየም ለመጫወት መስማማቱን ገልፀዋል፡፡ በአሰልጣኝ ቦቢ ዊሊያምሰን የሚመራው የኬኔያ ብሄራዊ ቡድን ዛሬ ወይ ነገ አዲስ አባባ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ኬኒያ በሳምንቱ መጨረሻ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ብራዛቪል ላይ ከኮንጎ ጋር አቻ መለያየቷ የሚታወስ ነው፡፡ ለዕሁዱ ጨዋታ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ለመውሰድ እንደተዘጋጀ ፌድሬሽኑ አክሎ ገልጿል፡፡ ሩዋንዳ ለምታዘጋጀው የቻን 2016 ለማለፍ ዋሊያዎቹ የሃራምቤ ከዋክብቶቹን በመጪው ዕሁድ የሚያስተናግዱ ይሆናል፡፡

ያጋሩ