ኢትዮዽያ ቡና እና ስራ አስኪያጁ ተለያይተዋል

ኢትዮጵያ ቡና  ክለቡን በዋና ስራ አስኪያጅነት በመምራት ለአንድ አመት የቆዩት አቶ በላይ እርቁ ከክለቡ ጋር መለያየታቸውን ሶከር ኢትዮጵያ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ምንጮች አረጋግጣለች፡፡

አቶ በላይ ከክለቡ ጋር የመለያየታቸው ምክንያት ምን እንደሆነ ለማወቅ ያደረግነው ጥረት ያልተሳካ ሲሆን ወደፊት ክለቡ በዚህ ጉዳይ የሚሰጠው ማረጋገጫ የሚጠበቅ ይሆናል፡፡ ሆኖም አሰልጣኝ ድራጋን ፖፓዲችን ወደ ክለቡ የመመለስ ሒደት ለመለያየታቸው ምክንያት ሊሆን እንደሚችል እየተነገረ ይገኛል።

በዘንድሮ የውድድር አመት ኢትዮዽያ ቡና ስፖርት ክለብ ደጋፊዎቹን በስፖርታዊ ጨዋነት ዙርያ ያዘጋጀው ጥናታዊ ፁሁፍ ፣ በቅርብ ቀን ይጀምራል ተብሎ የሚጠበቀው የቲቪ ፕሮግራም ፣ ሰኔ 25 የክለቡን አቅም ለማጠናከር የሚደረገው ሩጫ እንዲሁም የስታድየም ግንባታ እቅድ   ዲዛይን በዘንድሮ አመት የሰራቸው አበይት ስራዎች ቢሆኑም በውጤት ማጣት ፣ በተደጋጋሚ አሰልጣኝ በማሰናበት እና አስተዳደራዊ አለመረጋጋት ውስጥ ሆኖ የውድድር ዘመኑን ለመጨረስ ተቃርቧል።

1 Comment

Leave a Reply