ሳሙኤል ሳኑሚ ወደ ግብፅ ሊያመራ ይችላል

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን የኮከብ ግብ አግቢነት በ22 ግቦች የወሰደው ናይጄሪያዊው የደደቢት አጥቂ ሳሙኤል ሳኑሚ በግብፅ አል መስሪ ክለብ ውስጥ በሙከራ ላይ ይገኛል፡፡ የሳኑሚ ወኪል ቶፕ አላቢ እንደለፀው ከሆነ የሙከራ ጊዜው የታሳካ ከሆነ የሳኑሚ ቀጣይ ማረፊያ ግብፅ ናት፡፡

“ሳሙኤል ሳኑሚ በግብፅ አል መስሪ ክለብ ውስጥ ይገኛል፡፡ ለሰባት ቀናት የሙከራ ጊዜ ያሳልፋል፡፡ ለክለቡ የሚሰራ ወኪል ነው ነገሮችን ያመቻቸው፡፡ ሁኔታዎች ጥሩ ከሆኑ ሳሚ ለአል መስሪ የሚፈርም ይሆናል፡፡” ብለዋል ቶፕ አላቢ፡፡

ሳኑሚ በውድድሩ አመቱ በሁሉም ውድድሮች ላይ 27 ግቦችን እስቆጥሯል፡፡ በአፍሪካ ኮንፌድሬሽን ካፕ ላይ ሶስት ግቦችን ማስቆጠር ችሏል፡፡

 

ያጋሩ