ፊፋ በየሁለት ዓመቱ የሚያዘጋጀው የዓለም ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ዋንጫ የማጣርያ ድልድል ይፋ ሆኗል፡፡ ፈረንሳይ በምታስተናግደው የአለም ዋንጫ ለመሳተፍ በሚደረገው ማጣርያ በአንደኛወ ዙር መሳተፍ የምትጀምረው ኢትዮጵያ ከኬንያ እና ቦትስዋና አሸናፊን በመግጠም የማጣሪያ ጉዞዋን የምትጀምር ይሆናል፡፡
በ2016 በተካሄደው ዓለም ሴቶች ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ዋንጫ ፓፑዋ ኒው ጊኒ ስታስተናግድ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዞን ማጣሪያ እስከመጨረሻው ዙር ደርሳ በጋና የ6-2 ሽንፈት ገጥሟት ወደ ውድድሩ ሳታቀና መቅረቷ የሚታወስ ነው፡፡ በአሁኑ ማጣሪያ በቅድመ ማጣሪያ ዙር የሚገናኙትን ቦትስዋና እና ኬንያን አሸናፊ በመግጠም ውድድሩን ትጀምራለች፡፡
ቡድኑ ባላለፍነው የማጣሪያ ውድድር ባስለመዘገበው የተሻለ ውጤት ከቅደመ ማጣሪያው በቀጥታ ወደ አንደኛው ዙር አምርቷል፡፡ ከአንደኛው ዙር ማለፍ ከቻለችም የጋና እና አልጄሪያን አሸናፊ በሁለተኛው ዙር ትገጥማለች፡፡ ቡድኑ በዚህኛው ዙር ድል ከቀናው የጊኒ/ ካሜሮን እና ቱኒዚያ (ሊቢያ እና ሴራሊዮን) በመጨረሻው ዙር ይገጥማል፡፡
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በአሰልጣኝ አስራት አባተ እየተመራ በ2015ቱ የማጣሪያ ውድድር ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ ችሏል፡፡ በሎዛ አበራ ፊት አውራሪነት ቡድኑ በአጠቃላይ ውጤት ካሜሮን 2-1 እና ቡርኪናፋሶን 2-0 ማሸነፍ ሲችል በጋና 6-2 ተሸንፎ ከውድድር ቢወጣም አቅም ያለቸው ሴት ተጫዋቾች በማጣሪያው ጉዞ ታይተውበታል፡፡ ሎዛ አበራም በማጣሪያው 6 ግቦችን በማስቆጠር የማጣሪያው ኮከብ አግቢ ነበረች፡፡
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን የአዲስ አሰልጣኝ ቅጥር ጉዳይን በቅርብ ቀናት እንደሚያከናውን ይጠበቃል፡፡
* በማጣሪያው ሁለት ሃገራት ብቻ ወደ የዓለም ዋንጫ ያልፋሉ፡፡
የማጣሪያው ጉዞ
የቅድመ ማጣሪያ ዙር ጨዋታዎች (ከሀምሌ 14-16 ባሉት ቀናት የመልስ ጨዋታዎች ከሀምሌ 28-30 ባሉት ቀናት)
ቡሩንዲ ከ ጅቡቲ
ሊቢያ ከ ሴራሊዮን
ቦትስዋና ከ ኬንያ
የአንደኛ ዙር ጨዋታዎች
የአንደኛ ዙር ጨዋታዎች (መስከረም 5-7 2010 ባሉት ቀናት የመልስ ጨዋታዎች ከመስከረም 19-21)
የቡሩንዲ/ጅቡቲ ከ ሩዋንዳ (ጨዋታ 1)
ደቡብ አፍሪካ ከ ናሚቢያ (ጨዋታ 2)
ሞሮኮ ከ ሴኔጋል (ጨዋታ 3)
ናይጄሪያ ከ ታንዛኒያ (ጨዋታ 4)
ቱኒዚያ ከ ሊቢያ/ሴራሊዮን (ጨዋታ 5)
ጊኒ ከ ካሜሮን (ጨዋታ 6)
አልጄሪያ ከ ጋና (ጨዋታ 7)
ኢትዮጵያ ከ ኬንያ/ቦትስዋና (ጨዋታ 8)
የሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች (ከጥቅምት 24-26 ባሉት ቀናት የመልስ ጨዋታዎች ከህዳር 8-10 ባሉት ቀናት)
የጨዋታ 1 አሸናፊ ከ ጨዋታ 2 አሸናፊ (ጨዋታ 9)
የጨዋታ 3 አሸናፊ ከ ጨዋታ 4 አሸናፊ (ጨዋታ 10)
የጨዋታ 5 አሸናፊ ከ ጨዋታ 6 አሸናፊ (ጨዋታ 11)
የጨዋታ 7 አሸናፊ ከ ጨዋታ 8 አሸናፊ (ጨዋታ 12)
ሶስተኛ ዙር ማጣሪያ ጨዋታዎች (ከጥር 4-6 ባሉት ቀናት የመልስ ጨዋታዎች ከጥር 18-20 ባሉት ቀናት)
የጨዋታ 9 አሸናፊ ከ ጨዋታ 10 አሸናፊ
የጨዋታ 11 አሸናፊ ከ ጨዋታ 12 አሸናፊ