ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ወደ ኮንጎ የሚያመሩ 18 ተጫዋቾች ታውቀዋል

በካፍ ቶታል ቻምፒየንስ ሊግ የምድቡን አራተኛ ጨዋታ ከኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊኩ ኤ ኤስ ቪታ ጋር ማክሰኞ ሰኔ 13 ከምሽቱ 12:00 ላይ የሚያደርገው ቅዱስ ጊዮርጊስ ዛሬ የመጨረሻውን ልምምድ አከናውኗል።

በዛሬው የመጨረሻ ልምምድ ላይ በጋራ ተደራጅቶ በፍጥነት የማጥቃት የመከላከል ስራ የልምምዳቸው አካል ነበር ። ከጉዳት ጋር በተያያዘ ግብ ጠባቂው ዘሪሁን ታደለ በሆድ ህመም ምክንያት በዛሬው ልምምድ ባይገኝም ህመሙ ለክፉ እንደማይሰጥና ወደ ኮንጎ እንደሚያቀና ለማወቅ ሲቻል ከቡድኑ ውስጥ በጉዳት ሮበርት ኦዶንካራ ብቻ የማይጓዝ ይሆናል ።

ወደ ኮንጎ የሚያቀኑት 18 ተጨዋቾች ስም ዝርዝር ይሄን ይመስላል

 

ግብ ጠባቂዎች

ዘሪሁን ታደለ  ፣ ፍሬው ጌታሁን

ተከላካዮች

ደጉ ደበበ ፣ አስቻለው ታመነ ፣ ሳላዲን በርጌቾ ፣ አበባው ቡጣቆ ፣ ፍሬዘር ካሳ ፣ መሀሪ መና

አማካዮች

ምንተስኖት አዳነ ፣ ተስፋዬ አለባቸው ፣ ምንያህል ተሾመ ፣ ናትናኤል ዘለቀ ፣ አብዱልከሪም ኒኪማ ፣ በኃይሉ አሰፋ

 

አጥቂዎች

አዳነ ግርማ ፣ ሳላዲን ሰኢድ ፣ ፕሪንስ ሴቬርሆ ፣ ቡሩኖ ኮኔ

 

 

የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ልዑካን ነገ ጠዋት ረፋድ ላይ ወደ ኮንጎ የሚያቀኑ ይሆናል።

የዛሬው የልምምድ ከተጠናቀቀ በኋላ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ነገ ወደ ኮንጎ ለሚጓዙት የቡድኑ አባላት በድል እንዲመለሱ  አስደሳች የሆነ የሽኝት ፕሮግራም አዘጋጅተውላቸው ነበር ።

 

Leave a Reply