የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የፕሪምየር ሊጉ 30ኛ ሳምንት መርሀ ግብርን ሲያወጣ ሰኔ 17 ቀን 2009 የሊጉ መዝጊያ ቀን መሆኑ ተረጋግጧል፡፡
8 ቡድኖች የመውረድ ስጋት ያለባቸው በመሆኑ ሁሉም ጨዋታዎች በተመሳሳይ ሰአት ቅዳሜ ሰኔ 17 የሚካሄዱ ሲሆን የኢትዮጵያ ቡና እና አርባምንጭ ከተማ ጨዋታ ሰበታ ሜዳ ላይ እንዲካሄድ ተወስኗል፡፡
መርሀግብሩ የሚከተለውን ይመስላል
ቅዳሜ ሰኔ 17 ቀን 2009
09:00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (አአ)
09:00 ድሬዳዋ ከተማ ከ ጅማ አባ ቡና (ድሬዳዋ)
09:00 ወላይታ ድቻ ከ ደደቢት (ሶዶ)
09:00 ሀዋሳ ከተማ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ (ሀዋሳ)
09:00 ወልዲያ ከ አአ ከተማ (ወልዲያ)
09:00 ኢትዮጵያ ቡና ከ አርባምንጭ ከተማ (ሰበታ)
09:00 አዳማ ከተማ ከ ፋሲል ከተማ (አዳማ)
09:00 ሲዳማ ቡና ከ መከላከያ (ይርጋለም)
*በ29ኛ ሳምንት ቀሪ አንድ መርሀ ግብር ደደቢት ከ ሲዳማ ቡና ረቡዕ 8:30 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡