በአርባምንጭ ከተማ እና ወላይታ ድቻ ጨዋታ ላይ የፎርፌ ውሳኔ ተሰጠ 

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 29ኛ ሳምንት አርባምንጭ ላይ ወላይታ ድቻ አርባምንጭ ከተማን 1-0  ማሸነፉ የሚታወስ ነው፡፡ ከጨዋታው ፍጻሜ በኋላ ወላይታ ድቻ በተጫዋች ተገቢነት ጉዳይ ከጨዋታው ፎርፌ ማግኘት ይገባናል ብለው ያቀረቡት ክስ በፌዴሬሽኑ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡

በጨዋታው ላይ የአርባምንጭ ከተማው ተከላካይ በረከት ቦጋለ በ5 ቢጫ ምክንያት ማረፍ ሲገባው በመሰለፉ ምክንያት ወላይታ ድቻዎች ክስ ያስመዘገቡ ሲሆን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽንም ክሱ አግባብ መሆኑን በመግለጽ ለወላይታ ድቻ ፎርፌ (3 ነጥብ እና 3 ንጹህ ጎል) እንዲሰጥ መወሰኑን በደብዳቤ አስታውቋል፡፡

ላለመውረድ በሚደረገው ትግል ውስጥ ተሳታፊ የሆነው ወላይታ ድቻ ፎርፌውን ተከትሎ የነበረው የግብ እዳ ከ10 ወደ 8 ቀሎለታል፡፡

1 Comment

Leave a Reply