ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ፡ ፕላቲኒየም ስታርስ እና ሴፋክሲየን አቻ ተለያይተዋል

በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የረቡዕ ብቸኛ ጨዋታ ሮያል ባፎኬንግ ስታዲየም ላይ ፕላቲኒየም ስታርስ እና ሴፋክሲየን 1 አቻ ተለያይተዋል፡፡ በመጀመሪያው አጋማሽ እምብዛም ማራኪ ያለነበረ እና ቀዝቃዛ ጨዋታ ሁለቱ ክለቦች አሳይተዋል፡፡ ቦንጊ ንቱሊ ፕላቲኒየምን በ58ኛው ደቂቃ ቀዳሚ ሲያደርግ ከደቂቃዎች በኃላ መሪነቱን ማጠናከር የሚችልበትን እድል አምክኗል፡፡ ከግቡ መቆጠር በኃላ ያሉትን አብዛኛውን ደቂቃዎች እንግዶቹ የአቻነት ግብ ፍለጋ ይበልጥ ተጭነው መጫወት ችለዋል፡፡ መሃር ሃኒቺ የአቻነቷን ግብ ለቱኒዚያው ክለብ ማስገኘት ችሏል፡፡

የፕላቲኒየም ስታርሱ ግብ ጠባቂ ምቦንጌኒ ምዚሜላ በቀሪዎቹ ደቂቃዎች ክለቡ አንድ ነጥብ ይዞ እንዲወጣ አስችሏል፡፡ ውጤቱ የፕላቲኒየም ስታርስን የኮንፌድሬሽን ዋንጫ ጉዞ መገባደጃን ያቀረበ ሲሆን ሴፋክሲየን ከምድብ መሪው ኤምሲ አልጀር ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አንድ ማጥበብ ችሏል፡፡ የስዋዚላንዱ ምባባኔ ስዋሎስ በአራት ነጥብ ሶስተኛ ሲሆን ፕላቲኒየም ስታርስ በሁለት ነጥብ የምድቡን ግርጌ ይዟል፡፡

 

የማክሰኞ ውጤቶች

ክለብ ሬክሬቲቮ ዶስፖርቲቮ ዱ ሊቦሎ 3-0 ዜስኮ ዩናይትድ

ሪቨርስ ዩናይትድ 2-1 ካምፓላ ሲቲ ካውንስል ኦቶሪቲ

ሆሮያ አትሌቲክ ክለብ 1-0 ሲኤፍ ሞናና

ሱፐርስፖርት ዩናይትድ 0-0 ቲፒ ማዜምቤ

ክለብ አፍሪካ 2-1 ፋት ዩኒየን ስፖርት

አል ሂላል አባያድ 2-1 ስሞሃ

ሞውሊዲያ ክለብ ደ አልጀር 2-1 ምባባኔ ስዋሎስ

 

የዕረቡ ውጤት

ፕላቲኒየም ስታርስ 1-1 ክለብ ስፖርቲፍ ሴፋክሲየን

 

ቀጣይ ጨዋታዎች

አርብ ሰኔ 23/2009

18፡00 – ስሞሃ ከ ዜስኮ ዩናይትድ

21፡00 – ሞውሊዲያ ክለብ ደ አልጀር ከ ፕላቲኒየም ስታርስ

ቅዳሜ ሰኔ 23/2009

15፡00 – ሆሮያ አትሌቲክ ክለብ ከ ሱፐርስፖርት ዩናይትድ

21፡00 – አል ሂላል ኦባያድ ከ ክለብ ሬክሬቲቮ ዱ ሊቦሎ

እሁድ ሰኔ 25/2009

15፡00 – ምባባኔ ስዋሌስ ከ ክለብ ስፖርቲፍ ሴፋክሲየን

16፡00 – ካምፓላ ሲቲ ካውንስል ኦቶሪቲ ከ ፋት ዩኒየን ሰፖርት

16፡00 – ሲኤፍ ሞናና ከ ቲፒ ማዜምቤ

16፡00 – ሪቨርስ ዩናይትድ ከ ክለብ አፍሪኬን

Leave a Reply