ሀላባ ከተማ ባቀረበው ይግባኝ ፎርፌ ተወሰነለት

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 28ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ጂንካ ላይ ጂንካ ከተማ ከ ሀላባ ከተማ ያሰደረጉት ጨዋታ በ62ኛው ደቂቃ በተነሳ ረብሻ መቋረጡን ተከትሎ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን ኮሚቴ በጂንካ ከተማ አባላት እና ክለቡ ላይ ቅጣት ማስተላለፉ የሚታወስ ነው፡፡ የተቋረጠው ጨዋታም ከቆመበት እንዲቀጥል ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡

ውሳኔውን ተከትሎ ሀላባ ከተማ ለፌዴሬሽኑ ባስገባው ይግባኝ መሰረት ጉዳዩ በድጋሚ ታይቶ በውሳኔው ላይ መሻሻል ተደርጓል፡፡ በዚህም መሰረት በሀላባ ከተማ 2-1 መሪነት የተቋረጠው ጨዋታ ለሀላባ ከተማ ፎርፌ (3 ነጥብ እና 3 ንፁህ ጎል) እንዲሰጥ ተወስኗል፡፡

ሀላባ ከተማ በምድብ ለ 47 ነጥብ እና 16 የግብ ልዩነት በመያዝ 5ኛ ደረጃ የነበረ ሲሆን የፎርፌ ውሳኔው ተከትሎ ነጥቡ 50 ሲደርስ የግብ ልዩነቱ 19 መድረስ ችሏል፡፡ በጨዋታው ላይ አንድ ጎል አስቆጥሮ የነበረው አጥቂው ዘካርያስ ፍቅሬ በፎርፌው ውሳኔ ምክንያት ጎሉ የማይፀድቅለት ቢሆንም በ20 ግቦች ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪቱን መምራቱን ቀጥሏል፡፡

በምድብ ለ የመጨረሻው ሳምንት ‹‹በርበሬዎቹ›› ወደ ሆሳዕና ተጉዘው ወደ ፕሪምየር ሊግ ለመግባት ለሚደረገው የመለያ ጨዋታ (ከምድብ ሀ 2ኛ ደረጃ ከሚይዝ ቡድን ጋር የሚደረግ ጨዋታ) ለመድረስ እጅግ ወሳኝ ጨዋታ ከሀድያ ሆሳዕና ጋር የሚያደርጉ ይሆናል፡፡

የደረጃ ሰንጠረዡ ከፎርፌው ውሳኔ በኋላ ይህንን ይመስላል

7 Comments

  1. እኔ የምልው ይህ ውሳኔ ለምን በመቀሌ ላይ አልተወሰነም? ከዚህ በላይ መናጋር አይኖሮብኝም! ይህ ጥያቄ ለሁላችሁም ነው፡፡ ጋዜጠኖችስ ለምን አልጤቁም?

  2. halabawoch bzu endatguagu mnm tesfa ylachum hossana b 9 tchawach enkuan begba k 4 yalanse gole agbto endmeyashnf mnm altratrem tesfam ylachu

  3. መቼም ጊዜው ባለገንዘብ ጉልበቱን የሚያሳይበት ነው:: ክለቡን ያለጥፋቱ ገንዘብ ስለሌለው… እሱ ይሁን ጊዜው ነው(ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ… እንደሚባለው) ግን አትዬን ለምን?? አንድ ሰው ከሰውም ሰው ተገኘ ብንል ጂንካ በመጫወቱ ብቻ መቀጣት አለበት? ኧረ SHAME ነው! እግር ኳስ ፌደሬሽናችን ደሞ እያረፈ ነው እንዴ እንትን የሚለው? ኧረ ፋራ!!!!!!!

  4. መቼም ጊዜው ባለገንዘብ ጉልበቱን የሚያሳይበት ነው:: ክለቡን ያለጥፋቱ ገንዘብ ስለሌለው… እሱ ይሁን ጊዜው ነው(ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ… እንደሚባለው) ግን አትዬን ለምን?? አንድ ሰው ከሰውም ሰው ተገኘ ብንል ጂንካ በመጫወቱ ብቻ መቀጣት አለበት? ኧረ SHAME ነው! እግር ኳስ ፌደሬሽናችን ደሞ እያረፈ ነው እንዴ እንትን የሚለው? ኧረ ፋራ!!!!!!!

  5. ፌደረሽኑ የቤት የቤት ጨዋታ ተያይዞታል ….. እረ በእውቀት ይመራ ….. ዳኛው ላይ ምን ተወሰነ ?

Leave a Reply