የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ቀጣይ መርሀ ግብሮች ላይ የቀን ለውጥ ተደረገባቸው

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ ላይ ባሉት ተስተካካይ ጨዋታዎች ምክንያት ቀጣይ ጨዋታዎች ላይ መሸጋሸግ ተደርጓል፡፡ 

በምድብ ሀ 23ኛ ሳምንት መቀለ ከተማ ከ ባህርዳር ከተማ የተቋረጠው ጨዋታ እንዲሁም በ28ኛ ሳምንት ላይ ሳይደረጉ የቀሩት የአማራ ውሀ ስራ እና መቀለ ከተማ ፤ የባህርዳር ከተማ እና ሽረ እንዳስላሴ ጨዋታዎች ከዚህ በታች ባሉት ቀናት እንደሚደረጉ የኢትየጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ያወጣው መርሀግብር ያሳያል፡-

ረቡዕ ሰኔ 21 ቀን 2009

04:00 መቀለ ከተማ ከ ባህርዳር ከተማ (አአ ስታድየም)

እሁድ ሰኔ 25 ቀን 2009

08:00 ባህርዳር ከተማ ከ ሽረ እንዳስላሴ (አአ ስታድየም)

10:00 አማራ ውሀ ስራ ከ መቀለ ከተማ (አአ ስታድየም)

 

ከላይ በተጠቀሱት ጨዋታዎች ምክንያት የተሻሻለው የ30ኛ ሳምንት መርሀ ግብር የሚከተለውን ይመስላል፡፡

*የወሎ ኮምቦልቻ እና ሽረ እንዳስላሴ ጨዋታ ሀሙስ ሰኔ 29 ይደረጋል

በምድብ ለ የሚደረጉት ሁለት ወሳኝ ጨዋታዎች ከምድብ ሀ ጋር በተመሳሳይ ጊዜ እንዲጠናቀቁ በሚል ወደ ሰኔ 29 ተገፍተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *