የጥሎማለፉ የሩብ ፍጻሜ ዛሬ ጨዋታዎች ለሌላ ጊዜ ተሸጋገሩ

በኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ሩብ ፍጻሜ ዛሬ ሊደረጉ የነበሩት የአአ ከተማ እና ጅማ አባ ቡና ፤ ወላይታ ድቻ ከ ኤሌክትሪክ ጨዋታ ወደሌላ ጊዜ መሸጋገራቸው ታውቋል፡፡ የተሸጋገረበት ምክንያት በይፋ ባይገለፅም የስታድየሙ ሜዳ መጎዳት ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡

በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ቅዳሜ ለሚያደርገው ጨዋታ ሜዳው ጉዳት እንዳይደርስበት የሚያሳሳብ ደብዳቤ ለፌዴሬሽኑ ማስገባቱ የሚታወስ ሲሆን ሜዳው በተከታታይ ቀናት ከጣለው ዝናብ በተጨማሪ የጥሎ ማለፍ እና ከፍተኛ ሊግ ጨዋታ አስተናግዶ ይበልጡኑ ለመጫወት አስቸጋሪ ሆኗል፡፡

ፌዴሬሽኑ ጨዋታው መቼ እንደሚደረግ ያላሳወቀ ሲሆን በሁኑ ወቅት ከተጋጣሚዎቹ ክለቦች ጋር ውይይት ላይ መሆኑ ታውቋል፡፡

Leave a Reply