የከፍተኛ ሊግ የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታዎች ተራዘሙ

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 30ኛ ሳምንት ላይ ሰኔ 29 ሊደረጉ የነበሩ ጨዋታዎች ወደ ሐምሌ 3 መሸጋገራቸው ታውቋል፡፡ በምድብ ሀ የሚደረጉ ጨዋታዎች መጓተት ለመራዘሙ ዋንኛ ምክንያት ሆኗል፡፡

በምድብ ሀ ሱሉልታ ከተማ ከ መቀለ ከተማ ሰኞ ሊጫወቱ የነበረው ጨዋታ ወደ ማክሰኞ ከዛም ወደ ረቡዕ መሸጋገሩን ተከትሎ በሌሎች ተስተካካይ ጨዋታዎች ነርሀ ግብር ላይ መፋለስ አስከትሏል፡፡ ትላንት መደረግ የነበረበት የመቀለ ከተማ እና ባህርዳር ከተማ ጨዋታ ወደ ሰኔ 27 ሲሸጋገር ሰኔ 29 ሊደረጉ የነበሩት 4 ጨዋታዎችም ወደ ሐምሌ 3 ተሸጋግረዋል፡፡ የምድብ ለ ወሳኝ ጨዋታዎችም በተመሳሳይ ሐምሌ 3 የሚደረጉ ይሆናል፡፡

Leave a Reply