ፌዴሬሽኑ በሱሉልታ ላይ ቅጣት ሲያስተላልፍ መቀለ ከተማ ፎርፌ ተወሰነለት 

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 28ኛ ሳምንት ጨዋታ ረቡዕ ሰኔ 21 ቀን 2009 አአ ስታድየም ላይ በሱሉልታ ከተማ እና መቀለ ከተማ መካከል የተደረገው ጨዋታ በመቀለ ከተማ 1-0 መሪነት እሰከ 69ኛው ደቂቃ ተጉዞ የሱሉልታ ከተማ ተጫዋቾች በእለቱ ዳኛ ደረጀ ገብሬ ውሳኔዎች ላይ ተቃውሟቸውን በመግለፅ አቋርጠው ከሜዳ መውጣታቸው የሚታወስ ነው፡፡

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጉዳየዩ በተከሰተበት እለት ጨዋታውን በመራው ፌዴራል ዳኛ ንጉሴ ገብሬ ላይ የአንድ አመት እገዳ ማስተላለፉ የሚታወስ ሲሆን በተቋረጠው ጨዋታ ላይ በወሰነው ውሳኔ ሱሉልታ ከተማ ጨዋታውን አቋርጠው በመውጣታቸው የ50ሺህ ብር ቅጣት ተላልፎባቸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ለተጋጣሚው መቀለ ከተማ ፎርፌ (3 ነጥብ እና 3 ጎል) እንዲሰጥ መወሰኑ ታውቋል፡፡

ውሳኔውን ተከትሎ ከመሪው ወልዋሎ በ10 ነጥብ ርቀ የነበረውና ሁለት ተስተካካይ ጨዋታ የሚቀረው መቀለ ከተማ ልዩነቱን ወደ 7 ማጥበብ ችሏል፡፡