የአልጄሪያው ኤምሲ አልጀር ፕላቲኒየም ስታርስን 2-0 በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍፃሜ ማለፉን ያረጋገጠ የመጀመሪያው ክለብ ሆኗል፡፡ ተሸናፊው ፕላቲኒየም ስታርስ ከውድድሩ የተሰናበተበትን ውጤት ከአልጀር ይዞ ወጥቷል፡፡ ዜስኮ ዩናይትድን ያስተናገደው ስሞሃ 1-1 በሆነ ውጤት ጨዋታውን አጠናቋል፡፡
በጨዋታው ተመጣጣኝ ፉክክር የታየ ሲሆን እንግዶቹ በኳስ ቁጥጥር በጨዋታው የመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች ተሸለው ታይተዋል፡፡ አብደራህማን ሃሹድ በፍፁም ቅጣት ምት ኤምሲ አልጀርን ቀዳሚ ማድረግ ችሏል፡፡ ፍፁም ቅጣት ምቱ የተሰጠው ዛካሪያ መንሱሪ ላይ በተሰራ ጥፋት ቢሆንም ጥፋቱ አጥቂው ላይ የተሰራው ከፍፁም ቅጣት ምት ክልሉ ውጪ ነበር፡፡ ፕላቲኒየም ስታርሶች አቻ መሆን የሚችሉበትን ወርቃማ እድል አግኝተው ፋውዚ ካውቺ ኳስን ግብ ከመሆን ታድጓል፡፡ በጨዋታው መገባደጃ ደቂቃ ላይ ሂሻም ኔቃች በቮሊ ያስቆጠረው ግሩም ግብ በአልጄሪያ ከፍተኛ ተከታይ ያለው ክለብ ለድል አብቅቷል፡፡ ከምድብ ሁለት 11 ነጥቦችን የሰበሰበው ኤምሲ አልጀር ከወዲሁ ወደ ሩብ ፍፃሜ ማለፉን ሲያረጋግጥ የቱኒዚያው ሴፋክሲየን በ7 ነጥብ ይከተላል፡፡
በምድብ ሶስት አሌክሳንደሪያ ላይ ዜስኮ ዩናይትድን የገጠመው ስሞሃ በመጨረሻ ደቂቃ በተቆጠረ ግብ አቻ ተለይቷል፡፡ በጨዋታው ተመጣጣን ፉክክር የታየ ሲሆን በ84ኛው ደቂቃ ኬንያዊው ኢንተርናሽናል ጄሲ ጃክሰን ዌሬ በጥሩ የመልሶ ማጥቃት የመጣውን ኳስ ወደ ግብ የሞከረውን ኳስ የስሞሃውን ተጫዋች ያስር ኢብራሂም በራሱ ግብ ላይ አስቆጥሮ ዜስኮን ለወሳኝ ድል የሚያበቃ ቢመስልም ቡርኪናፋሶዋዊ ባኑ ዲያዋራ ስሞሃን ከመሸነፍ ያዳነች ግብ በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሯል፡፡ ምድቡን አሁንም የሱዳኑ አል ሂላል ኦባያድ በ7 ነጥብ ሲመራ ወሳኝ ነጥብ ከግብፅ ይዞ የተመለሰው ዜስኮ መሪው ጋር በነጥብ መስተካከል ችሏል፡፡ ሬክሬቲቮ ሊቦሎ በስድስት ነጥብ ሶስተኛ ነው፡፡
ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ሲደረጉ ቀሪ አራት ጨዋታዎች እሁድ የሚደረጉ ይሆናል፡፡
የአርብ ውጤቶች
ስሞሃ 1-1 ዜስኮ ዩናይትድ
ሞውሊዲያ ክለብ ደ አልጀር 2-0 ፕላቲኒየም ስታርስ
የቅዳሜ ጨዋታዎች
15፡00 – ሆሮያ አትሌቲክ ክለብ ከ ሱፐርስፖርት ዩናይትድ
21፡00 – አል ሂላል ኦባያድ ከ ክለብ ሬክሬቲቮ ዱ ሊቦሎ
የእሁድ ጨዋታ
15፡00 – ምባባኔ ስዋሎስ ከ ክለብ ስፖርቲፍ ሴፋክሲየን
16፡00 – ካምፓላ ሲቲ ካውንስል ኦቶሪቲ ከ ፋት ዩኒየን ስፖርት
16፡00 – ሲኤፍ ሞናና ከ ቲፒ ማዜምቤ
16፡00 – ሪቨርስ ዩናይትድ ከ ክለብ አፍሪካ