‹‹ በናይሮቢ ውጤቱን እንቀለብሳለን ›› ቦቢ ዊልያምሰን

የኬንያው አሰልጣን ቦቢ ዊልያምሰን ከጨዋታው በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት አስተያየት በናይሮቢ በሚደረገው የመልስ ጨዋታ ውጤቱን እንደሚቀለብሱት ተስፋ አድርገዋል፡፡

‹‹ ጨዋታው ጥሩ እና የሚስብ ነበር፡፡ የፍፁም ቅታት ምት ባንስት ኖሮ ወደ ተከታዩ ዙር ለማለፍ ናይሮቢ ላይ 1-0 ማሸነፍ ይበቃን ነበር፡፡ 2-0 በመሸነፋችን ከአንድ በላይ ግብ ማስቆጠር ይጠበቅብናል፡፡ ሆኖም ከ14 ቀን በኋላ በምናደርገው ጨዋታ ውጤቱን ቀልብሰን ወደ ቀጣዩ ዙር እናልፋለን፡፡ ›› ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ያጋሩ