አልሜሪክ እና ሽመልስ በቀለ ተለያዩ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የአጥቂ አማካይ ሽመልስ በቀለ ከጥቂት ወራት የሱዳን ቆይታ በኋላ ከአልሜሪክ ጋር በስምምነት ተለያየ፡፡

የሊቢያው አል-ኢትሃድ ክለብን ለቆ ወደ ከ6 ወራት በፊት ወደ ሱዳኑ ታላቅ ክለብ ያመራው ሽመልስ በተዘዋወረበት ወቅት ከሜሪክ ጋር የተስማማውን ገንዘብ ክለቡ ሊሰጠው ባለመቻሉ በስምምነት ፊርማቸውን ቀደው ተጫዋቹም ነፃ (Free agent) ሆኗል፡፡ በመሆኑም በግሉ ተደራድሮ ከፈለገው ክለብ ጋር ውል የመፈራረም መብት አለው፡፡

ሽመልስ ከሱዳን መልስ ወዴት ሊያመራ እንደሚችል የተገለፅ ነገር የለም፡፡

ሌሎች አጫጭር ዜናዎች

· ኢትዮጵያ በወርሃዊው የፈፋ የሃገሮች ደረጃ 6 ደረጃዎችን ዝቅ ብላለች፡፡ በወሩ ውስጥ ምንም አይነት የወዳጅነት እና የነጥብ ጨዋታ ያላደረገችው ኢትዮጵ ባለፈው ከነበረችበት 101ኛ ደረጃ ወርዳ 107ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡

· የኢትዮጵ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ‹‹ ሉሲ ›› በነገው እለት ወደ አክራ ይበራል፡፡ በአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ማጣርያ የመጨረሻ ዙር ጨዋታ በሜዳው በጋና የ2-0 ሽንፈት የደረሰበት ቡድን አስቸጋሪውን የቤት ስራ ተወጥቶ ወደ ናሚቢያ ለማምራት የመጨረሻውን ትግል እሁድ ያደርጋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *